በናይጀሪያ ለደህንነቱ የሰጋ ፓስተር ክላሽ ይዞ መስበኩ አነጋጋሪ ሆኗል
ግለሰቡ አንዳንድ ሰዎች ሊያጠቁኝ እንደሚፈልጉ ተረድቻለሁ ብሏል
በናይጀሪያ ያለ ፖሊስ እውቅና የጦር መሳሪያ መታጠቅ አይቻልም
በናይጀሪያ ለደህንነቱ የሰጋ ፓስተር ክላሽ ይዞ መስበኩ አነጋጋሪ ሆኗል።
በምዕራብ አፍሪካዊቷ ናይጀሪያ አንድ የክርስትና ሀይማኖት ሰባኪ ወይም ፓስተር ክላሽ ይዞ መታየቱ ብዙዎችን አስገርሟል።
- በናይጀሪያ ዩኒቨርሲቲዎች እየደረሰ ያለው ጾታዊ ትንኮሳ አሳሳቢ ነው ሲሉ ፕሬዝደንት ሁሃሪ ተናገሩ
- አሜሪካ የአደጋ ጊዜ ያልሆኑ ሰራተኞች ናይጀሪያን ለቀው እንዲወጡ ፈቀደች
ኡቼ አግቤ የተሰኘው ይህ ናይጀሪያዊ በአቡጃ ለደህንነቴ ሰግቻለሁ በሚል ክላሽ ታጥቆ ወደ ቤተ ክርስቲያን መምጣቱን ቢቢሲ ዘግቧል።
"የተወሰኑ ሰዎች እኔን ማጥቃት ይፈልጋሉ፣ ስለዚህ ይህን ክላሽ ታጥቄ መጥቻለሁ" ሲል ለአምልኮ ወደ ቤተክርስቲያን ለመጡ ተከታዮቹ ተናግሯል ተብሏል።
በናይጀሪያ ህግ መሰረት አንድ ግለሰብ የጦር መሳሪያ መታጠቅ የሚችለው ከፖሊስ ፈቃድ ካገኘ ብቻ እንደሆነ ተገልጻል።
ይሁንና ይህ ፓስተር የጦር መሳሪያውን የታጠቀው በህጋዊ መንገድ ይሁን አይሁን እስካሁን አልታወቀም።
ግለሰቡ አክሎም ከጌታ ስልጣን የተሰጠን አገልጋዮች ህዝቡን የመጠበቅ ግዴታ ተጥሎብናል፣ የጦር መሳሪያ መታጠቄም በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያሉ ሰዎችን ደህንነት የመጠበቁ አካል ነው" ሲልም ለአምልኮ ለመጡ ናይጀሪያውያን ተናግሯል ተብሏል።
በናይጀሪያ ቦኮሀራም በሚል የሚታወቀው የሽብር ቡድን ብዙ አደጋዎችን በዜጎች ላይ በማድረስ ላይ ሲሆን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ የክርስትና ሀይማኖት ተከታዮች እና አገልጋዮች የጥቃቱ ኢላማ እየሆኑ ይገኛሉ።