ፖለቲካ
አሜሪካ የአደጋ ጊዜ ያልሆኑ ሰራተኞች ናይጀሪያን ለቀው እንዲወጡ ፈቀደች
ዜጎቿ እንዲወጡ የፈቀደችው በናይጀሪያ የሽብር ስጋት ስላለባቸው መሆኑን ገልጻለች
አሜሪካ እና እንግሊዝ በናይጀሪያ ዋና ከተማዋ አቡጃ የሽብር ጥቃት ሊደርስ እንደሚችል ማስጠንቀቃቸውን ይታወሳል
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለአደጋ ጊዜ ከሚያስፈልጉ ሰራተኞች ውጭ ያሉት በናይጀሪያ የሚገኙ አሜሪካ መንግስት ሰራተኞች እና ቤተሰቦቻቸው ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ ፈቀደ
አሜሪካ ዜጎቿ እንዲወጡ የፈቀደችው በናይጀሪያ የሽብር ስጋት ስላለባቸው መሆኑን ገልጻለች፡፡
በቅርቡ አሜሪካ እና እንግሊዝ በናይጀሪያ ዋና ከተማዋ አቡጃ በተለይም በመንግስት ህንጻዎች፣ የአምልኮ ቦታዎች እና ትምህርት ቤቶች ላይ ያነጣጠረ የሽብር ጥቃት ሊደርስ እንደሚችል ባለፈው እሁድ ማስጠንቀቃቸውን ተከትሎ ነው፡፡
"በናይጄሪያ አቡጃ ያለው የአሜሪካ ኢምባሲ ላሉ የአሜሪካ ዜጎች የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ የመስጠት አቅሙ ውስን" ነው ብሏል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ፡፡
የናይጄሪያ ስቴት ሰርቪስ ዲፓርትመንት አሜሪካ ከዚህ ቀደም ተመሳሳይ ማስጠንቀቂያ ሰጥታ እንደነበር ገልጾ ዜጎቹ ነቅተው እንዲጠብቁ አሳስቧል።
በአብዛኞቹ የናይጄሪያ ግዛቶች የተስፋፋው የጸጥታ ችግር በመጪው የካቲት ወር አዲስ ፕሬዚዳንት በሚመርጡ መራጮች የሚነሳ ዋነኛው ጉዳይ ነው።