በናይጀሪያ ዩኒቨርሲቲዎች እየደረሰ ያለው ጾታዊ ትንኮሳ አሳሳቢ ነው ሲሉ ፕሬዝደንት ሁሃሪ ተናገሩ
መንግስት ችግሩን ለማስወገድ አልቻለም የሚል ትችት ቀርቦበታል
ፕሬዝደንት ቡሀሪ በዩኒቨርሲቲዎች ከሚፈጸሙት ሙስናዎች ውስጥ ጾታዊ ጥቃት ከፍተኛ መጠን የሚይዝ ነው ብለዋል
የናይጀሪያው ፕሬዝደንት ሙሃመድ ቡሃሪ በትናንትናው እለት እንደተናገሩት በናይጀሪያ ዩኒቨርሲቲዎች እየተፈጸመ ያለው ጾታዊ ትንኮሳ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡
ፕሬዝደንቱ በተደረገው ምርምራ “ወሲብን ነጥብ ለማግኘት” የመጠቀም ተግባር እየተፈጸመ ያለ የሙስና አካል ነው ማለታቸውን ሮይርስ ዘግቧል፡፡
በፈረንጆቹ 2019 ቢቢቢ ያደረገው የምርመራ ዘገባ በናይጀሪያ በሁለት ዩኒቨርሲቲዎች የሚደረጉትን ጾታዊ ትንኮሳዎች አጋልጦ ነበር፤ ዘገባውን ተከትሎም በናይጀሪያ “ወሲብን ለነጥብ” የሚል ክርክር ፈጥሮ ነበር፡፡
ከዚያ ወዲህ ብዙም ለውጥ አለመኖሩን እና መንግስት ችግሩን ለማስወገድ አልቻለም የሚል ትችት ቀርቦበታል፡፡
ነበርግን ፕሬዝደንት ቡሃሪ በአቡጃ በተካሄደው የጸረ መስና ስብሰባ ላይ መንግስት የጾታዊ ጥቃት ጉዳይ እንዳሳሰበው እና የሀገሪቱ ነጻ የሙስና ተግባራት ኮሚሽን በዩኒቨርሲቲዎች የሚፈጸሙ ጥቃት ላይ ክስ እየመሰረተ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ፕሬዝደንት ቡሃሪ ምን ያህል ሰዎች እንተከሰሱ ግን አልገለጹም፡፡ ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲ ካፓሶች ውስጥ የተለያዩ የሙስና አይነቶች እንዳሉ ይገልጻሉ ያሉት ፕሬዝደንቱ ነጥብ ለማግኘት ገንዘብ መክፈል እና ወሲብ መፈጸም እና የፈተና መስረቅ ሞናውን ጠቅሰዋል፡፡
ፕሬዝደንት ቡሀሪ በዩኒቨርሲቲዎች ከሚፈጸሙት ሙስናዎች ውስጥ ጾታዊ ጥቃት ከፍተኛ መጠን የሚይዝ ነው ብለዋል፡፡
በናይጀሪያ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የሚያስተምሩ መምህራን የተሸለ ደሞዝ እና አበል ይከገለን በማት ለሰባት ወራት ያህል አድማ ላይ ናቸው፡፡ፕሬዝደንቱ ቡሃሪ በማይሆን ምክንያት አድማ ያደረጉ መመህራን መንግስት በትምህርት ላይ እያደረገ ያለውን ኢንቭስትመንት እየጎዱት ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡