የ19 የአሜሪካ እና የካናዳ ዩኒቨርሲቲዎችን የትምህርት ዕድል ያሸነፈችው ናይጄሪያዊት
ለዚህ ዕድል ያበቃት በምዕራብ አፍሪካ የከፍተኛ ትምህርት ፈተናን በከፍተኛ ውጤት በማጠናቀቋ ነው ተብሏል
ቪክትሪ ዪንካ በአጠቃላይ ከ5 ሚሊዮን ዶላር በላይ ዋጋ አላቸው የተባለላቸውን የትምህርት ዕድሎች ነው ያሸነፈችው
የ17 ዓመቷ ናይጀሪያዊት 19 የአሜሪካ እና የካናዳ ዩኒቨርሲቲዎችን የትምህርት ዕድል (ስኮላር ሺፕ) አሸነፈች።
ቪክትሪ ዪንካ የተባለችው የ17 ዓመቷ ናይጀሪያዊት 19 የአሜሪካ እና የካናዳ ዩንቨርሲቲዎች ሙሉ ስኮላርሺፕ አሸንፋለች።
ተማሪዋ በአጠቃላይ ከ5 ሚሊዮን ዶላር በላይ ዋጋ ያላቸው የመጀመሪያ ድግሪ ሙሉ ስኮላርሺፕ አሸንፋለች።
እንደ ሲኤንኤን ዘገባ ከሆነ ናይጀሪያዊቷ ተማሪ ቪክትሪ ዪንካ ታዋቂው ሃርቫርድ ዩንቨርሲቲን ጨምሮ ፕሪንስተን ብራውን ዩንቨርሲቲ ፤ ማሳቹስቲስ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ጆን ሆፕኪንስ ዩንቨርሲቲ፣ ስታንድፎርድ ዩንቨርሲቲ እና ሌሎች ታዋቂ የአሜሪካን እና የካናዳ ዩኒቨርሲቲዎች የሙሉ ስኮላርሺፕ እድል አግኝታለች።
ተማሪዋ ስኮላርሺፑን ለማግኘት ያበቃት የምዕራብ አፍሪካ ከፍተኛ ተምህርት ፈተናን ሁሉንም ኤ በማምጣቷ ነው።
“ስኮላርሺፑን አሸንፋለሁ ብዬ አላሰብኩም ነበር” የምትለው ተማሪ ቪክትሪ በትምህርት እድሉ ደስተኛ መሆኗን ተናግራ በቀጣይ ተጨማሪ ጥናቶችን ካደረገች በኋላ የምትማርበትን ዩኒቨርሲቲ እንደምትወስንም ገልጻለች።
ዩኒቨርሲቲዎቹ እንዳጠና ያቀረቡልኝ እድል አጓጊ ቢሆንም ባዮሎጂ የማጥናት አቅድ አለኝ የምትለው ቪክትሪ ስኮላርሺፖቹን ማሸነፌ የበለጠ በራሴ እንድተማመን አድርጎኛልም ብላለች።
ለዚህ ስኬት የበቃችው በርትታ በማጥናቷ እና በወላጆቿ ብርቱ ድጋፍ እና ጥሩ ስነ ምግባር ስላላት መሆኑንም ጨምራ ገልጻለች።