ቻይናውያኑ በፍንዳታ ምክንያት በቆፈሩት ጉድጓድ ውስጥ ለመቆየት ተገደው ከነበሩት 22 ማዕድን ቆፋሪዎች መካከል ናቸው
በምስራቃዊ ቻይና ሻንዶንግ ግዛት በወርቅ ማዕድን ቁፈራ ላይ ሳሉ ጉድጓድ ተደርምሶ ያለፉትን ሁለት ሳምንታት በምድር ከርስ ውስጥ ለማሳለፍ ተገደው የነበሩት11 ቻይናውያን ከጉድጓድ በህይወት ወጡ፡፡
በህይወት ቆይተው ምድርን ለማየት ከበቁት 11 ቻይናውያን መካከል 10ሩ ማዕድን ቆፋሪዎች ናቸው፡፡
አንደኛው ለከፍተኛ ጉዳት በመጋለጡ ምክንያት ወዲያውኑ ወደ ሆስፒታል ተወስዷል፡፡
ቻይናውያኑ የማዕድን ማውጫ ስፍራው ከ15 ቀናት በፊት ባጋጠመው ፍንዳታ ምክንያት ነበር በምድር ከርስ ውስጥ ለማሳለፍ ተገደው የቆዩት፡፡
በወቅቱ 22 ቻይናውያን ነበሩ በተደረመሰው ጉድጓድ ውስጥ ለመቆየት የተገደዱት፡፡
ቀደም ሲል በተደረገው ከፍተኛ ርብርብ 10ቹን በህይወት ለመታደግ ተችሎ ነበረ፡፡ በመልካም አካላዊ እና አዕምሯዊ ደህንነት ይዞታ ላይ ይገኙ የነበረ መሆኑን ተከትሎም ትናንት ጭምር በጉድጓድ ውስጥ ለመቆየት ተገደው የነበሩ ባልደረቦቻቸውን የማፈላለጉን ተግባር ሲያግዙ አቅጣጫዎችንም ሲጠቁሙ ነበር፡፡
በዚህም እስከ ዛሬ በህይወት ለመቆየት ችለው ከጉድጓዱ የወጡትን ማዕድን ቆፋሪዎች ለመታደግ ተችሏል፡ ሆኖም አንድ የቆፋሪዎቹ ባልደረባ በጭንቅላቱ ላይ በደረሰበት ከፍተኛ ጉዳት ምክንያት ህይወቱ አልፏል፡፡
ቻይናውያኑን ለማትረፍ 600 ገደማ የነፍስ አድን ሰራተኞች ተሰማርተዋል፡፡ አዲስ የተቆፈሩትን 2 ጉድጓዶች ጨምሮ 12 ጉድጓዶች መቆፈራቸውንም ሰራተኞቹ አስታውቀዋል፡፡ጉድጓዶቹ ለቆፋሪዎቹ ምግብ እና መድሃኒት ሌሎችም ሰብዓዊ ድጋፎች የሚደርሱባቸው ናቸው፡፡