ደቡባዊ የአፍሪካ ክፍል ከ4 የአፍሪካ ቀጣናዎች በቀዳሚነት በኮሮና መጠቃቱን የማእከሉ ሪፖርት ያሳያል
በአፍሪካ በኮሮና የተያዙ ሰዎች ቁጥር 3.4 ሚሊዮን መድረሱን የአፍሪካ የበሽታ መቆጣጠርና መከላከል ማእከል አስታውቋል፡፡ እንደ ማእከሉ መረጃ በአሀጉሪቱ 83 901 ሰዎች በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው አልፏል፡፡
በቫይረሱ ከተያዙት ሰዎች መካከል 2.8 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች ማገገም መቻላቸውን ማእከሉ አስታውቋል፡፡ ደቡባዊው የአፍሪካ ክፍል ከሁሉም የአፍሪካ ቀጣናዎች በከፍተኛ መጠን መጠቃቱን የማእከሉ ሪፖርት ያመለክታል፡፡
ከአፍሪካ ሀገራት መካከል በከፍተኛ መጠን ከተጠቁት ሀገራት መካከል ደቡብ አፍሪካ፣ሞሮኮ፣ ቱኒዚያና ኢትዮጵያ በቅደምተከተል እንደሆኑ ማእከሉ ያሳያል፡፡ በኮቪድ-19 በከፍኛ ደረጃ የተጎዳችው ደቡብ አፍሪካ ከ40ሺ በላይ ሰዎች ህይወታቸውን አጥተውባታል፡፡
የኮሮና ቫይረስ በታህሳስ 2012 ዓ.ም ነበር በቻይና ተከሰተው፤ ከቻይና የተነሳው ኮሮና መላውን አለም በማዳረስ የማህበራዊ፣ፖለቲካዊ እንዲሁም የኢኮኖሚ ቀውስን አስከትሏል፡፡