ሰሜን ኮሪያ ማስጠንቀቂያውን ወደ ጎን በመተው ሁለት ባለስቲክ ሚሳይሎችን አስወነጨፈች
ሰሞኑን በሰሜን ኮሪያ ተቀናቃኞች ላይ ስጋት መፍጠሩን ሮይተርስ ዘግቧል
ሰሜን ኮሪያ፤ አሜሪካ እና ደቡብ ኮሪያ የሚያደርጓቸውን የጋራ ወታደራዊ ልምምዶችን "ቀስቃሽ" በማለት የተቃውሞ ሰልፍ አድርጋለች
የደቡብ ኮሪያ ጦር እንዳስታወቀው ሰሜን ኮሪያ በምስራቅ የባህር ዳርቻዋ ሁለት የአጭር ርቀት ባለስቲክ ሚሳይሎችን አስወነጭፋለች፡፡
ሰሞኑን በሰሜን ኮሪያ ተቀናቃኞች ላይ ስጋት መፍጠሩን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
ሰሜን ኮሪያ አዲስ ሚሳይል ሙከራ በተለይም የባላስቲክ ሚሳይሎችን እና የአጭር ርቀት ሚሳይሎችን ሙከራ ለማድረግ በሂደት ላይ መሆና በደቡብ ኩሪያ እና አጋሮቿ ላይ ስጋት ማሳደሩ ተገልጿል፡፡
ሁለቱ ሚሳኤሎች፤ የደቡብ ኮሪያ የጋራ የጦር አዛዦች እንደገለጹት የአጭር ርቀት ሚሳይሎች ሲሆኑ ሰሜን ኮሪያ ምስራቃዊ የባህር ጠረፏ ላይ በካንግዎን ግዛት ከምትገኘው ቶንግቾን የተወነጨፉ ናቸው፡፡
ሰሜን ኮሪያ ሁለቱን ሚሳይች ያስወነጨፈችው ደቡብ ኮሪያ እና አሜሪካ ካሰሙት የማስጠንቀቂያ ተኩስ አራት ቀናት በኋላ ነው ተብሏል፡፡
የደቡብ ኮሪያ ጦር በሰጠውመግለጫ ከቅርብ አጋሮች ጋር በቅርበት በመቀናጀት የክትትል እና የደህንነት እርምጃዎችን ከማጠናከር በተጨማሪ "ሙሉ ዝግጁነት ሁነታ" ውስጥ እንደሚቆይ ገልጿል፡፡
አሜሪካ እና ደቡብ ኮሪያ እያካሄዱ ያሉትን ወታደራዊ ልምምዶችን በዛሬው እለት የሚያጠናቅቁ ሲሆን ሁለቱ ሀገራት በሚቀጥለው ሰኞ ሌሎች ልምምዶችን ይጀምራሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ሰሜን ኮሪያ፤ አሜሪካ እና ደቡብ ኮሪያ የሚያደርጓቸውን ተከታታይ የጋራ ወታደራዊ ልምምዶችን "ቀስቃሽ" በማለት የተቃውሞ ሰልፍ አድርጋለች፡፡ ሰሜን ኮሪያ ይህን ልምምድ "ግዛቷን ለመውረር" የሚደረግ እንደሆነ አድርጋ ትቆጥረዋለች፡፡