ሰሜን ኮሪያ ለመጀመረያ ጊዜ 'ኑክሌር ተሸካሚ ባህር ስርጓጅ መርከብ' ይፋ አደረገች
ደቡብ ኮሪያ እና አሜሪካ በደህንነቷ ላይ ስጋት እንደደቀኑባት በተደጋጋሚ የምትገልጸው ሰሜን ኮሪያ የሚሳይል ሙከራዎችን በተደጋጋሚ ታደርጋለች
ተንታኞች እንደሚሉት ይህ ባህር ሰርጓጅ መርከብ የተሻሻለ የሶቬት ዘመን የጦር መርከብ ይመስላል ይላሉ
ሰሜን ኮሪያ ለመጀመሪያ ጊዜ ታክቲካል ኑክሌር ተሸካሚ ባህር ስርጓጅ የጦር መርከብ ይፋ አድርጋለች።
ሀገሪቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ይፋ ያደረገችው እና ወደ ስራ ያስገባችው ይህ የጦር መርከብ በኮሪያ ፔንዙላ እና በጃፖን መካከል ያለውን ባህረሰላጤ ለሚጠብቀው ቡድን መሰጠቱ ተገልጿል።
ሰርጓጅ መርከብ ቁጥር 841 ኪም ኩን በተባለ በጀግና እና ታሪካዊ የሰሜን ኮሪያ መሪ ስም የተሰየመ ሲሆን ዋነኛ የባህር ውስጥ ማጥቂያ እንደሚሆን የሰሜን ኮሪያ መሪ ኪም ጆንግ ኡን ስራ ባስጀመሩበት ወቅት ተናግረዋል።
ተንታኞች እንደሚሉት ይህ ባህር ሰርጓጅ መርከብ የተሻሻለ የሶቬት ዘመን የጦር መርከብ ይመስላል ይላሉ።
መርከብ 10 የመተኮሻ ቀዳዳዎች ያሉት ሲሆን ባለስቲክ ሚሳይና እና ክሩዝ ሚሳይል ታጥቆ ሊሆን እንደሚችል ተንታኞች ተናግርዠረዋል።
የደቡብ ኮሪያ ጦር ይፋ የሆነው ባህር ሰርጓጅ የጦር መርከብ ለመደበኛ ውጊያ ዝግጁ የማይመስል እና ሰሜን ኮሪያ ያላትን ወታደራዊ አቅም ማጋነኗን የሚያሳዩ ምልክቶች ናቸው ብሏል።
ደቡብ ኮሪያ እና አሜሪካ በደህንነቷ ላይ ስጋት እንደደቀኑባት በተደጋጋሚ የምትገልጸው ሰሜን ኮሪያ የሚሳይል ሙከራዎችን በተደጋጋሚ ታደርጋለች።
ሰሜን ኮሪያ፣ ደቡብ ኮሪያ ከአጋሯ አሜሪካ ጋር በመሆን የምታደርገውን ወታደራዊ ልምምድ እንደትንኮሳም ትቆጥረዋለች፤ ለአጸፋ ሚሳይሎችንም ትተኩሳለች።