ሰሜን ኮሪያ ወደ ግዛቷ ለገባው ኮሮና ቫይረስ ጎረቤቷን ተጠያቂ አደረገች
ኮሮና ከተከሰተ ሁለት ዓመት ያለፈው ሲሆን በሰሜን ኮሪያ መኖሩ ይፋ የሆነው ከአንድ ወር በፊት ነው
ሰሜን ኮሪያ የኮሮና ቫይረስ ወደ ግዟቷ የገባው ከደቡብ ኮሪያ በገቡ ፊኛዎች አማካኝነት መሆኑን ገልጻለች
ሰሜን ኮሪያ ወደ ሀገሯ ለገባው ኮሮና ቫይረስ ጎረቤቷን ተጠያቂ አደረገች፡፡
ሚሳኤሎችን በማስወንጨፍ የምትታወቀው ሰሜን ኮሪያ በቅርቡ የኮሮና ቫይረስ ወደ ሀገሯ እንደገባ መግለጿ መናገሯ ይታወቃል፡፡
ሀገሪቱ ዛሬ ባወጣችው መግለጫ ወደ ሀገሯ ለገባው የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ጎረቤቷ ደቡብ ኮሪያን ተጠያቂ አድርጋለች፡፡
ሰሜን ኮሪያ እንዳለችው የኮሮና ቫይረስ ወደ ሀገሯ የገባው የኮሮና ቫይረስ ከደቡብ ኮሪያ በአንድ አክቲቪስት አማካኝነት በተለቀቀ ፊኛዎች አማካኝነት እንደሆነ ተገልጿል፡፡
የሀገሪቱ ባለስልጣናት ተናገሩት ብሎ ቪኦኤ እንደዘገበው ከሆነ ባለፈው ሚያዝያ ወር ላይ በሁለቱ ኮሪያዎች ድንበር ላይ የ18 ዓመት የደቡብ ከሪያ ወታደር የአምስት ዓመት ሰሜን ኮሪያዊ በአካል በማግኘቱ እና ፊኛውን ለልጁ በመስጠቱ ቫይረሱም በዚህ መንገድ ወደ ሀገሯ እንደገባ ተገልጿል፡፡
የኮሮና ቫይረስ በሰሜን ኮሪያ ከተሞች መስፋፋቱን ተከትሎም የሀገሪቱ ባለስልጣናት በደቡብ ኮሪያ ላይ መበሳጨታቸው የተገለጸ ሲሆን ቀጥሎ ምን ሊመጣ እንደሚችል ደቡብ ኮሪያዊያን በስጋት ላይ ናቸው ተብሏል፡፡
ሰሜን ኮሪያ የኮሮና ቫይረስ ወደ ሀገሯ ሊገባ የሚችለው በድንበር ዘለል ወፎች፣በበረዶ እና በአየር ንብረት ብክለት ሊሆን እንደሚችል ስጋት የነበራት ቢሆንም ቫይረሱ ባላሰበችው መንገድ ወደ ሀገሯ እንደገባ አስታውቃለች፡፡
ባሳለፍነው ሳምንት አንድ ደቡብ ከሮያዊ በ20 ፊኛዎች አማካኝነት የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ወይም ማስክን ጨምሮ የኮሮና ቫይረስን ለማከም የሚውሉ የተለያዩ ቫይታሚኖችን እና ሌሎች ቁሳቁሶችን ወደ ሰሜን ኮሪያ መላኩ ተገልጿል፡፡
ኮሮና ቫይረስ በዓለም ላይ ከተከሰተ ሁለት ዓመት ያለፈው ሲሆን በሰሜን ኮሪያ ግን ቫይረሱ በይፋ ከተረጋገጠ አንድ ወር አልፎታል፡፡
የጤና ባለሙያዎች ግን ሰሜን ኮሪያ የቫይረሱን ባህሪ እና የስርጭት ሁኔታ ላይረዱት እንደሚችሉ እና ከቁጥጥር ውጪ ከመሆኑ በፊት የዓለም ጤና ድርጅት ድጋፍ እና ክትትል ሊያደርግ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡