ጃፓን ሰሜን ኮሪያን ለማናገር ደጅ የምትጠናው ለምንድ ነው?
የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ፉሚዮ ኪሽዳ ያለምንም ቅደመ ሁኔታ ከሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ጋር መነጋገር እንደሚፈልገለ ተናግረዋል
የሰሜን ኮሪያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቾይ ፒዮንግያንግ ከቶኪዮ ጋር መነጋገር አትፈልግም ብለዋል
ጃፓን ሰሜን ኮሪያን ለማናገር ደጅ የምትጠናው ለምንድ ነው?
ሰሜን ኮሪያ ከጃፓን ጋር ንግግር ማድረግ እንደማትፈልግ የሰሜን ኮሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቾይ ሰን ሁይ መናገራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ፉሚዮ ኪሽዳ ያለምንም ቅደመ ሁኔታ ከሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ጋር መነጋገር እንደሚፈለጉ እና ይህን ከ20 አመት በኋላ የመጀመሪያ የሚሆነውን ንግግር እውን ለማድረግ የሚደረገውን ጥረት በግላቸው እንደሚከታተሉ ተናግረዋል።
ነገርግን ቾይ ሰሜን ኮሪያ ከጃፓን መሪዎች ጋር የመገናኘት ፍለጎት እንደሌላት እና በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የሻከረ ግንኙነት የማደስ ፍላጎት እንደሌላት አመልክተዋል።
ቾይ አክለውም ፒዮንግያንግ በታገቱ ጃፓናውያን ጉዳይ ለመተባበር ፍቃደኛ አለመሆኗን እና ሉአላዊነቷን ጥሳ ጣልቃ በገባችው ጃፓን ላይ ጠንካራ ምላሽ እንደምትሰጥ ተናግረዋል።
የጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር በማይሆን ነገር ላይ የሙጥኝ ለምን እንዳሉ እንዳልገባቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቾይ ተናግረዋል።
በፈረንጆቹ 2002 ሰሜን ኮሪያ ከአስር አመት በፊት 13 ጃፓናውያንን ማገቷን አምናለች። ቆየት ብለው ወደ ጃፓን የተመለሱት አምስት ታጋቾች እና ቤተሰቦቻቸው ሌሎቹ መሞታቸውን ተናግረዋል።
ነገርግን 17 ጃፓናውያን ታግተዋል ብላ የምታምነው ቶኪዮ ያልተመለሱትን እጣፈንታ ለማወቅ ምርመራዋን መቀጠሏን የጃፓን ሚዲያዎች እየዘገቡ ዘግበዋል።
በቻይና የሰሜን ኮሪያ አምባሳደር የሆኑት ራይ ሪዮንግ ከጃፓን ጋር በየትኛውም ደረጃ ውይይት እንደማይደረግ መናገራቸውን ዘገባው ጠቅሷል።
ራይ አክለው በቤጂንግ የሚገኘው የጃፓን ኢምባሲ ባለስልጣን ግንኙነት ለማድረግ ለሰሜን ኮሪያ ኢምባሲ የኢሜል መልእክት መላካቸውምን ተናግራዋል።
ተጽዕኖ ፈጣሪዋ የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን እህት ኪም ዮ ጆንግ ጃፓን በባለፈው ታሪክ ሳትታጠር በአዲስ ምዕራፍ ግንኙነት ለመጀመር ዝግጁ ከሆነች ንግግር ማድረጉን እንቀበላለን ብለዋል።
በጃፓን እና ሰሜን ኮሪያ መካከል ያለው ግንኙነት የሻከረው በ2000ዎቹ መጀመሪያ ሰሜን ኮሪያ ጃፓናውያንን በማገቷ እና 1910-1945 ባለው ጊዜ ጃፓን የኮሪያን ባህረ ሰላጤ ወርራ በማያዟ እና ኃይል ተጠቅማ ወሲባዊ ባርነት በመፈጸሟ ነው።
ጃፓን እና ሰኮሪያ፣ በፒዮኔግያንግ የኑክሌር መርሀግብር ላይም ተጋጭተዋል።