ሩሲያ እና ሰሜን ኮሪያ የጦር መሳሪያ ግብይታቸው መድራቱን አሜሪካ ገለጸች
ሰሜን ኮሪያ ሩሲያ በዩክሬን ለጀመረችው ዘመቻ የተተኳሽ ድጋፍ እያደረገች ነው ተብሏል
የሩሲያ ከፍተኛ በለስልጣናት ወደ ፒዮንግዮንግ በመመላለስ ላይ እንደሆኑ ተገልጿል
ሩሲያ እና ሰሜን ኮሪያ የጦር መሳሪያ ግብይታቸው መድራቱን አሜሪካ ገለጸች፡፡
ሲኤንኤን የአሜሪካ ስለላ መረጃዎችን ዋቢ አድርጎ አንደ ዘገበው ሩሲያ እና ሰሜን ኮሪያ የጦር መሳሪያ ሸመታቸው ደርቷል ተብሏል፡፡
የሁለቱ ሀገራት የጦር መሳሪያ ግብይት አሳስቦኛል ያለችው አሜሪካ የሩሲያ ከፍተኛ ባለስልጣናት ወደ ሰሜን ከሪያ መዲና በተደጋጋሚ እየተጓዙ እንደሆነም ገልጻለች፡፡
የሩሲያ መከላከያ ሚኒስትር ሰርጊ ሼጉ ወደ ፒዮንግያንግ ተጉዘው ከፕሬዝዳንት ኪም እና ሌሎች ወታደራዊ መሪዎች ጋር መክረው ተመልሰዋል፡፡
እንዲሁም ተጨማሪ የሩሲያ ወታደራዊ ልኡክ ወደ ሰሜን ኮሪያ በማምራት ተጨማሪ ትብብሮች እና ውይይቶችን አድርጎ መመለሱን የዋሸንግተን የስለላ ሪፖርት ላይ ተጠቅሷል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ፕሬዝዳንት ፑቲን እና ኪም ጆንግ ኡን የሁለቱን ሀገራት ትብብሮች እና ወዳጅነት የሚያሳድጉ ደብዳቤዎችን እንደተለዋወጡ ዋሸንግተን አስታውቃለች፡፡
ሩሲያ በዩክሬን ለጀመረችው ወታደራዊ ዘመቻ የተተኳሽ እጥረት ገጥሟታል የምትለው አሜሪካ ሰሜን ኮሪያ የጦር መሳሪያ ድጋፍ በማድረግ ላይ ነችም ስትል ከሳለች፡፡
ኖርዎይ ወደ ሩሲያ ይሄዳሉ በሚል ስጋት በርካታ አጋዘኖችን አረደች
በቀጣዮቹ ወራትም ሁለቱ ሀገራት በከፍተኛ መሪዎች ደረጃ የሚያደርጓቸው ውይይቶች እና ትብብሮች ሊቀጥሉ እንደሚችሉም በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡
በተለይም ሁለቱ ሀገራት የጦር መሳሪያ ማምረቻ ኢንዱስትሪ ግብዓት ሊለዋወጡ እንደሚችሉ የተገለጸ ሲሆን አሜሪካ ሰሜን ኮሪያ ከዚህ ድርጊቷ እንድትታቀብ አስጠንቅቃለች፡፡
እንደ አሜሪካ የስለላ መረጃ ከሆነ ሩሲያ የጦር መሳሪያ እጥረት የገጠማት ሲሆን ሞስኮ ይህንን ችግሯን ለመፍታት ከኢራን እና ሰሜን ኮሪያ በመግዛት ላይ ትገኛለች፡፡