ሰሜን ኮሪያ ቆሻሻ የያዙ ፊኛዎችን ወደ ደቡብ ኮሪያ መላኳን እንደ አዲስ ቀጠለች
ደቡብ ኮሪያ ከሁለት ቀናት በፊት ለሰሜን ኮሪያ ዶላርና በራሪ ወረቀቶችን የያዙ ፊኛዎች ልካለች
ፒዮንግያንግ ፀረ ሰሜን ኮሪያ በራሪ ወረቀቶች መላካቸውየማይቆም ከሆነ ቆሻሻ መላኩ እንደሚቀጥል አስጠንቅቃለች
ሰሜን ኮሪያ ቆሻሻ ያዙ ፊኛዎችን ወደ ደቡብ ኮሪያ መላክ መቀጠሏ ተነግሯል።
ቆሻሻ ያዙ በርካታ የሰሜን ኮሪያ ፊኛዎች በደቡብ ኮሪያ ዋና ከተማ ሴኡል እና ሌሎች የድንበር አካባቢዎች ላይ ሌሊቱን እንዲሁም ዛሬ ማለዳ ላይ መውደቃቸው ተንግሯል።
ቆሻሻ ያየዙ ፊኛዎች ሴኡልውስጥ የወደቁት የደቡብ ኮሪያ ጦር ትናንት ቅዳሜ ምሽት ሰሜን ኮሪያ ፊኛዎቹን በድጋሚ እየላከቻቸው መሆኑን መግለጹን ተከትሎ ነው።
የደቡብ ኮሪያ ጦር ዛሬ በወጣው መግለጫውም፤ የፊኛዎችን ጉዳይ በጣም በጥነቃቄ እና በትኩረት እንደሚከታተለው በመግለጽ፤ እንደ አስፈላጊነቱ እርምጃ እንደመወስድ ገልጿል።
ቆሻሻ የያዙ ፊኛዎች የተላኩባት ደቡብ ኮሪያ በሰሜን ኮሪያ ላይ “የማይቋቋሙት” እርምጃዎችን እንደምትወስድ የዛተች ሲሆን፣ ይህም ወደ ሰሜን አቅጣጫ በተዘጋጁት ግዙፍ የድምፅ ማጉያዎች የፕሮፓጋንዳ ስርጭቶችን ሊያካትት ይችላተብሏል።
የሰሜን ኮሪያ መንግስት በበኩሉ ቆሻሻ ያዙ ፊኛዎቹ የተላኩት የደቡብ ኮሪያ አክቲቪስቶች ለላኩት የፀረ ሰሜን ኮሪያ በራሪ ወረቀት የያዙ ፊኛዎች ምለሽ መሆኑን አስታውቋል።
ሰሜን ኮሪያ ለደቡብ ኮሪያ ምላሽ በፈረንጆቹ ግንቦት መጨረሻ ላይ በጣም አጸያፊ ቆሻሻዎችን ያዙ በመቶዎች የሚቆጠሩ ፊኛዎችን መላኳም ይታወሳል።
በፈረንጆቹ ሰኔ 2 ላይ ወደ ደቡብ ኮሪያ ቆሻሻ የያዙ ፊኛዎችን መላኳን በጊዜያዊነት ማቆሟን ያስታወቀችው ሰሜን ኮሪያ፤ ምክንያቱ ደግሞ የተላው 15 ቶን ቆሻሻ ለተላከባት የፕሮፖጋዳ ፊኛ በቂ መልሽ ይሆናል ብላ ስለምታምን እንደሆነም አስታውቃ ነበር።
ይሁን እንጂ ከሁለት ቀናት በፊት በደቡብ ኮሪያ የሚገኝ የማህበረሰብ አንቂ ቡድን ወደ ሰሜን ኮሪያ ሙዚቃዎች፣ ዶላርና በራሪ ወረቀቶችን የያዙ ፊኛዎችን መላኩ ይታወሳል።
ለሰሜን ኮሪያ ነጻነት እታገላለሁ የሚለው ቡድን፥ 200 ሺህ በራሪ ወረቀቶችን፣ 5 ሺህ የደቡብ ኮሪያ ኬ-ፖፕ ሙዚቃና ድራማዎች የተጫኑባቸው ፍላሾች እንዲሁም 2 ሺህ የ1 ዶላር ኖቶች በ10 ፊኛዎች ከድንበር ከተማዋ ፖቺዮን ወደ ሰሜን ኮሪያ ልኳል።
ይህንን ተከትሎም ሰሜን ኮሪያ ወደ ደቡብ ኮሪያ ቆሻሻ ያዙ ፊኛዎችን ዳግም መላክ እንድትጀምር እንዳደረጋ ነው የተነገረው።
ሰሜን ኮሪያ ባሳለፍነው ሳምንት ውስጥ 15 ቶን የሚመዝኑ ቆሻሻዎችን በ3 ሺህ 500 ፊኛዎች ወደ ደቡብ ኮሪያ መላኳ ይታወሳል።
በድንበር ከተማዎች ውጥረት የፈጠረው ክስተት ሴኡል ከፒዮንግያንግ ጋር በ2018 የደረሰችውን ወታደራዊ ስምምነት አቋርጣ በድንበር አካባቢ ወታደራዊ ልምምድ እንድትጀምር ማድረጉም አይዘነጋም።