ደቡብ ኮሪያ ከሰሜን ኮሪያ ጋር የገባችውን ወታደራዊ ስምምነት ልታቋርጥ እንደምትችል አስጠነቀቀች
ጽ/ቤቱ ይህን ያለው ሴኡል ቆሻሻ የተሞሉ ፊኛዎችን ለላከችባት ፒዮንግያንግ ጠንካራ ምላሽ እንደምትሰጥ ከዛተች በኋላ ነው።
ሰሜን ኮሪያ በመቶዎች የሚቆጠሩ ቆሻሻ የያዙ ፊኛዎችን ድንበር አቋርጠው በደቡብ ኮሪያ ግዛት እንዲያርፉ ማድረጓን ደቡብ ኮሪያ እንደትንኮሳ እንደምትመለከተው ገልጻለች
ደቡብ ኮሪያ ከሰሜን ኮሪያ ጋር የገባችውን ወታደራዊ ስምምነት ልታቋርጥ እንደምትችል አስጠነቀቀች።
በፈረንጆቹ 2018 ደቡብ ኮሪያ ከሰሜን ኮሪያ ጋር የተፈራረመችውን ውጥረትን የማርገብ ወታራዊ ስምምነት ለማቋረጥ ማቀዷን የሀገሪቱ ፕሬዝደንት ጽ/ቤት አስታውቋል።
ጽ/ቤቱ ይህን ያለው ሴኡል ቆሻሻ የተሞሉ ፊኛዎችን ለላከችባት ፒዮንግያንግ ጠንካራ ምላሽ እንደምትሰጥ ከዛተች በኋላ ነው።
ሰሜን ኮሪያ በመቶዎች የሚቆጠሩ ቆሻሻ የያዙ ፊኛዎችን ድንበር አቋርጠው በደቡብ ኮሪያ ግዛት እንዲያርፉ ማድረጓን ደቡብ ኮሪያ እንደትንኮሳ እንደምትመለከተው ገልጻለች።
የደቡብ ኮሪያ ብሔራዊ የጸጥታ ምክር ቤት እንደገለጸው ወታደራዊ ስምምነቱን የማቋረጥ እቅዱን ለማጸደቅ በነገው እለት በሚካሄደው የፓርላማ ስብሰባ እንደሚቀርብ ገልጿል።
ስምምነቱ የሚቋረጥ ከሆነ በድንበር አቅራቢያ ወታደራዊ ልምምድ ለማድረግ እና ለሰሜን ኮሪያን ትንኮሳዎች" በቂ እና አፋጣኝ እርምጃ" ለመውሰድ ያስችላል ብሏል ምክር ቤቱ።
ምክርቤቱ ሊወሰድ ያሰበው እርምጃ ምን እንደሆነ አላብራራም።
በ2018 በሁለቱ ኮሪያዎች መካከል በተካሄደው ታሪካዊ ጉባኤ የተደረሰው ስምምነት ባለፈው አመት በሰሜን ኮሪያ ተጥሷል። ሰሜን ኮሪያ በስምምነቱ እንደማትገዛ ግልጽ አድርጋለች።
ውሉን አክብረን የምንቀጥል ከሆነ "በወታራዊ ኃይላችን ዝግጁነት ላይ ችግር ሊፈጥር ይችላል" ሲል ምክርቤት ጠቅሷል።
ሰሜን ኮሪያ፣ ደቡብ ኮሪያ እና ዋነኛ አጋራ አሜሪካ በኮሪያ ባሆረ ሰላጤ የሚያደርጉት ወታደራዊ ልምምድ ለደህንነቷ ስጋት እንደሆነባት በተደጋጋሚ ገልጻለች።
ደቡብ ኮሪያ እና አሜሪካ ከሰሜን ኮሪያ ሊቃጣ የሚችል ጥቃት ለመመከት ወታራዊ የትብብር ስምምነትም አላቸው።