ሰሜን ኮሪያ ከሰሞኑን ያስወነጨፍኳቸው ሚሳይሎች የማስመሰል ጥቃቶች ናቸው አለች
ደቡብ ኮሪያ ባለፈው ሳምንት የወረዱባትን የሚሳይል ክፍሎች እየለቃቀመች ነው
የደቡብ ኮሪያ እና የአሜሪካ ባለስልጣናት ፒዮንግያንግ የኒውክሌር መሳሪያን ለመሞከር ዝግጅት እያደረገች ነው ብለዋል
ሰሜን ኮሪያ በቅርቡ የወሰደችው የሚሳይል ጥቃት በደቡብ ኮሪያ እና አሜሪካ ላይ የማስመሰል ጥቃት መሆኑን ተናግራለች።
ሁለቱ ሀገራት አደገኛ የጦር ልምምድ እያደረጉ ነውም ብላለች።
የሰሜን ኮሪያን ጓዳዋ የደረሱ ሚሳይል ስብርባሪዎችን ከባህር ዳርቻዋ አካባቢ ማግኘቷን ተናግራለች።
ባለፈው ሳምንት ደቡብ ኮሪያ እና አሜሪካ ቅዳሜ ዕለት የተጠናቀቀ የስድስት ቀናት የአየር ልምምዶች ሲያደርጉ ሰሜን ኮሪያ በርካታ ሚሳይሎችን አስወንጭፋለች።
ከእነዚህም ውስጥ ሮይተርስ በዘገባው ያልተሳካ አህጉር አቋራጭ ሚሳኤል እና በመቶዎች የሚቆጠሩ የመድፍ ቀልሀ ወደ ባህር ውስጥ ገብተዋል።
የሰሜን ኮሪያ ጦር “የጥቃት አውሎ ነፋስ” ልምምዶች “ሆን ብሎ ውጥረቱን ለማባባስ ያለመ ግልጽ ቅስቀሳ” ነው ያለ ሲሆን፤ “በጣም ከፍተኛ ጠበኛ ተፈጥሮ ያለው አደገኛ የጦርነት ልምምድ” ነው ብሏል።
የሀገሪቱ ጦር በአየር ሰፈሮች እና አውሮፕላኖች ላይ እንዲሁም በደቡብ ኮሪያ ዋና ከተማ ላይ "የጠላቶችን የማያቋርጥ የጦርነት ወዳድነት ለመምታት" ጥቃቶችን የማስመሰል እንቅስቃሴዎችን አድርጌለሁ ነው ያለው።
የሚሳይል ማስወንጨፉ በአንድ ቀን ውስጥ እጅግ ብዛት ያለውና ኒውክሌር የታጠቀችው ሰሜን ኮሪያ የሚሳይል ሙከራዋ ክብረ ወሰን በተሻገረበት ዓመት የተፈጸመ ነው።
የደቡብ ኮሪያ እና የአሜሪካ ባለስልጣናት ፒዮንግያንግ የኒውክሌር መሳሪያን ለመሞከር ዝግጅት እያደረገች ነው ብለዋል። ይህም ሙከራ ሰሜን ኮሪያ ከፈረንጆቹ 2017 በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የምታደርገው ሙከራ መሆኑ ታውቋል።
አሜሪካ ፣ጃፓን እና የደቡብ ኮሪያ ከፍተኛ ዲፕሎማቶች እሁድ እለት በስልክ መነጋገራቸውን የጠቀሰው የሮይተርስ ዘገባ፤ ባለፈው ሳምንት በደቡብ ኮሪያ የባህር ዳርቻ ላይ ያረፈው ሚሳይል "በግድየለሽነት" ማስወንጨፏን ጨምሮ የቅርብ ጊዜ ሙከራዎችን አውግዘዋል ሲል የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ ገልጿል።