ሰሜን ኮሪያ ከ100 በላይ መድፍ መተኮሷን ደቡብ ኮሪያ አስታወቀች
ፒዮንግያግ ሁለቱ ኮሪያዎች ከወታደራዊ ግጭት ነፃ ባደረጉት የድንበር አካባቢመድፎችን ተኩሳለች
ደቡብ ኮሪያ እና አሜሪካ ከሰሜን ኮሪያ ጋር የገቡት ፍጥጫ የቀጠናውን በጦርነት እንዳያምሰው ተሰግቷል
ሰሜን ኮሪያ በዛሬው እለት ከ100 በላይ መድፎችን መተኮሷን የደቡብ ኮሪያ ጦር አስታወቀ።
የደቡብ ኮሪያ ወታደራዊ መኮንኖች እንዳስታወቁት፤ ፒዮንግያንግ በዛሬው ሰሜን ኮሪያ ከደቡብ ጋር ባደረጉት ወታደራዊ ስምምነት ወደተቋቋመው ከወተደራዊ ግጭት ነፃ ቀጠና መድፎችን ተኩሳለች።
ሰሜን ኮሪያ ከመድፎቹ በተጨማሪም በዛሬው እለት የባለስቲክ ሚሳኤል የሞከረች ሲሆነ፤ ሚሳዔሉ ከደቡብ ኮሪያ የባህር ዳርቻ በ60 ኪሎሜትር ርቀት ማረፉም እየተነገረ ነው።
ይህም የመጀመሪያው መሆኑን የገለፀችው ሴኡል ከፒዬንግያንግ ጋር መፋጠጧ ነው የተሰማው።
የሰሜን ኮሪያ ተግባር በፈረንጆቹ 2018 የተደረሰውን ግጭት የማቆም ስምምነት እንደሚጥስ የደቡብ ኮሪያ መከላከያ ጠቅላይ ኢታማዦር መናገራቸውን ሬውተርስ አስነብቧል።
አሜሪካ እና ደቡብ ኮሪያ በትናትናው እለት በአይነቱ ግዙፍ የተባለ የአየር ኃይል ወታደራዊ ልምመድ መጀመራቸው ይታወቃል
የተባለለትንና አስከ አርብ ድረስ የሚቀጥል ግዙፍ የአየር ልምምድ ሁለቱ ሀገራት ስውር አውሮፕላኖችን ጨምሮ ከ240 በላይ አውሮፕላኖችን ከሰማይ በላይ በማሰባሰብ በኮሪያ ልሳነ ምድር ልምምዳቸው እያደረጉ ነው፡፡
አሜሪካ እና ደቡብ ኮሪያ የጀመሩት የአየር ኃይል የጋራ ወታደራዊ ልምምድ ሰሜን ኮሪያን ያስቆጣ ሲሆን፤ ባወጣችው የማስጠንቀቂያ መግለጫ በአሜሪካ እና በደቡብ ኮሪያ መካከል የሚደረገውን መጠነ ሰፊ የአየር ልምምድ “ግጭት ቀስቃሽ” ነው ብላለች።
ሀገራቱ ከድርጊታቸው የማይታቀቡ ከሆነ እርምጃ እንደመትወስድም ዛቻ አዘል መልእክት አስተላልፋች።
ሰሜን እና ደቡብ ኮሪያ በቅርቡ በአወዛጋቢው የባህር ድንበር አከባቢ ማስጠንቀቂያ የተኩስ ልውውጥ ማድረጋቸው ተከትሎ በሁለቱም ኮሪያዎች ግጭት ሊፈጠር እንደሚችል ሲዘገብ ቆይቷል።
እስካሁን በሁለቱም ኮሪያዎች መካካል ጦርነት መደረጉ የሚያመላክቱ ሪፖርቶች ባይኖሩም በኮሪያ ባረ ሰላጤ ምዕራባዊ የባሕር ዳርቻ ያለው የባህር ድንበር ለረጅም ጊዜ የዘለቀ ደህንነት ስጋት ምንጭ መሆኑ ይታወቃል።