ኢትዮ ቴሌኮም በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም የቴሌኮም አገልግሎት ያስጀመረባቸውን አካባቢዎችን ይፋ አደረገ
አላማጣ፣ ኮረም እና ዓዲ አርቃይ የቴሌኮም አገልግሎት ከተጀመረባቸው አካባቢዎች ውስጥ ተጠቃሽ ናቸው
በደቡብ አፍሪካ በተካሄደው ድርድር የተቋረጡ አገልግሎቶችን ማስጀመር ስምምነት ከተደረሰባቸው ነጥቦች ውስጥ አንዱ ነው
ኢትዮ ቴሌኮም በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም የቴሌኮም አገልግሎት ያስጀመረባቸውን አካባቢዎችን ይፋ አደረገ
አላማጣ፣ ኮረም እና ዓዲ አርቃይ የቴሌኮም አገልግሎት ከተጀመረባቸው አካባቢዎች ውስጥ ተጠቃሽ ናቸው
በደቡብ አፍሪካ በተካሄደው ድርድር የተቋረጡ አገልግሎቶችን ማስጀመር ስምምነት ከተደረሰባቸው ነጥቦች ውስጥ አንዱ ነው
ኢትዮ ቴሌኮም በሰሜን ኢትዮጵያ የቴሌኮም አገልግሎት ተቋርጦ ከነበረባቸው አካባዎች መካከል በተወሰኑት ዳግም የቴሌኮም አገልግሎት ማስጀመሩን አስታውቋል።
በኢትዮጵያ መንግስት እና በህወሓት መካከል በደቡብ አፍሪካ ሲካሄድ የነበረው የድርድር ውጤት በትናንትናው እለት ይፋ መደረጉ ይታወሳል።
በድርድሩ ስምምነት ከተደረሰባቸው ጉዳዮች ውስጥም የተቋረጡ መሰረታዊ አገልግሎቶችን መልሶ ማስጀመር የሚለው ተጠቃሽ ናቸው።
ኢትዮ ቴሌኮምም በዛሬው እለት በሰሜን ኢትዮጵያ የተከሰተውን ጦርነት ተከትሎ በትግራይ እና በአማራ ክልል የተወሰኑ አካባቢዎች ተቋርጦ የነበረውን የቴሌኮም አገልግሎት ዳም መስጀመሩን አስታውቋል።
ኢትዮ ቴሌኮም ፤ የቴሌኮም አገልግሎት ተቋርጦባቸው የነበሩና ዳግም ያስጀመረባቸውን አካባቢዎችን ዝርዝር ይፋ አድርጓል።
የቴሌኮም አገልግሎት የጀመረባቸው አካባቢዎች ፦
- አላማጣ
- ኮረም
- ዓዲ አርቃይ
- ጸለምት
- ጪሮ ለና
- ጎብዬ ቆቦ
- ቆቦ ሮቢጥ፣
- ዞብል
- ዋጃ መሆናቸውን ኢትዮ ቴለኮም በማህበራዊ ትስስር ገጾቹ ባጋራው መግለጫ አስታውቋል።
ኢትዮ ቴሌኮም በሌሎችም የቴሌኮም አገልግሎት በተቋረጠባቸው አካባቢዎች በቅርቡ አገልግሎት ለማስጀመር እየሠራ እንደሚገኝም አስታውቋል።