ኪም ጆንግ ኡን የሰሜን ኮሪያን የኑክሌር ጦር መሳሪያ በከፍተኛ ቁጥር ለመጨመር ዛቱ
አሜሪካን ከጎኗ ባለሰለፈችው እና በሩሲያ በምትደገፈው ሰሜን ኮሪያ መካከል ያለው ውጥረት ቋሚ ሆኖ ቀጥሏል
ኪም ጠንካራ ወታደራዊ አቋም "ከአሜሪካ እና አጋሮቿ የሚቃጣውን ከባድ ስጋት" ለመከላከል እንደሚያስችል ተናግረዋል
ኪም ጆንግ ኡን የሰሜን ኮሪያን የኑክሌር ጦር መሳሪያ በከፍተኛ ቁጥር ለመጨመር ዛቱ።
የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ሀገሪቱ ያላትን የኑክሌር ጦር መሳሪያ ቁጥር "በከፍተኛ ቁጥር" ለመጨመር የኑክሌር ኃይል ግንባታ ፖሊሲ እየተገበረች ነው ብለዋል።
ኪም በትናንትናው እለት በተካሄደው የሰሜን ኮሪያ የምስረታ በዓል ላይ ሀገሪቱ ጸጥታዋን ለማስጠበቅ የኑክሌር አቅሟን ማሳደግ እና በተፈለገ ጊዜ ለመጠቀም የሚያስችል ዝግጁነት ማድረግ አለባት ሲሉ መናገራቸውን ሮይተርስ የኮሪያውን ኬሲኤንኤን ጠቅሶ ዘግቧል።
ጠንካራ ወታደራዊ አቋም "ከአሜሪካ እና አጋሮቿ የሚቃጣውን ከባድ ስጋት" ለመከላከል እንደሚያስችል ኪም አክለው ገልጸዋል።
ኪም እንዳሉት ሰሜን ኮሪያ በቀጣናው ካለው በአሜሪካ ከሚመራው የኑክሌር ጥምረት ከባድ ስጋት ተጋርጦባታል። የደቡብ ኮሪያ የፖሊሲ ምክትል መከላከያ ሚኒስትር ቾ ቸንጅ ራይ፣ እና የአሜሪካ እና የጃፓን አቻዎቻቸውፒዮንግያንግ በቅርቡ እያደረገች ያለውን የኑክሌር ጦር መሳሪያ አይነት የማብዛት እና የባለስቲክ ጦር መሳሪያ ሙከራዎች በዛሬው እለት አውግዘዋል።
በሴኡል ስብሰባ ያደረጉት ሀገራቱ በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል ባወጡት የጋራ መግለጫ ከሰሜን ኮሪያ የሚቃጣውን የኑክሌር እና የሚሳይል ጥቃት ስጋት በመቀልበስ በቀጣናው ሰላም ለማስፈን በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል።
ሀገራቱ "የነጻነት አጥር" የተባለውን ሁለተኛውን የሶስትዮሽ ወታደራዊ ልምምድ ለማድረግ ተስማምተዋል። ደቡብ ኮሪያ የተመድ እዝ(ዩኤንሲ) አባል ከሆኑ ሀገራት የመከላከያ ሚኒስትሮች ጋር ስብሰባ ለማድረግ እቅድ ይዛለች።
ዩኤንሲ መቀመጫውን ደቡብ ኮሪያ ባደረገው የአሜሪካ ወታደራዊ ጣቢያ የሚመራ ነው። ባለፈው ወር ጀርመን ከፍተኛ ወታደራዊ ስምሪት ያለበትን ከሰሜን ኮሪያ ጋር ያለውን ድንበር የሚጠብቀውን እና ጦርነት በሚነሳ ጊዜ ደቡብ ኮሪያን የሚከላከለውን ዩኤንሲን ተቀላቅላለች።
ሰሜን ኮሪያ ዩኤንሲ "ህገወጥ የጦር ድርጅት" ስትል ተችታዋለች።
አሜሪካን ከጎኗ ባለሰለፈችው እና በሩሲያ በምትደገፈው ሰሜን ኮሪያ መካከል ያለው ውጥረት ቋሚ ሆኖ ቀጥሏል።