ሰሜን ኮሪያ ወታደራዊ ልምምድ በሚያደርጉት ላይ ያልተጠበቀ እርምጃ እወስዳላሁ ስትል አስጠነቀቀች
ሰሜን ኮሪያ በትብብር ወታደራዊ ልምምድ በሚያደርጉት ላይ ከዚህ ቀደም ታይቶ የማይታወቅ እርምጃ እወስዳላሁ ስትል አስፈራራች
አሜሪካን ጨምሮ የደቡብ ኮሪያ አጋሮች በቀጠናው ውጥረቱ እንዲፈጠር አድርገዋል በማለት ሰሜን ኮሪያ እየከሰሰች ነው
ሰሜን ኮሪያ ወታደራዊ ልምምድ በሚያደርጉት ላይ ያልተጠበቀ እርምጃ እወስዳላሁ ስትል አስጠነቀቀች።
በትብብር ወታደራዊ ልምምድ በሚያደርጉት ላይ ከዚህ ቀደም ታይቶ የማይታወቅ እርምጃ እወስዳላሁ ስትል አስፈራራች።
ሰሜን ኮሪያ እንዳለችው ደቡብ ኮሪያ እና አሜሪካ በታቀዱ ወታደራዊ ልምምዶች ወደፊት የሚራመዱ ከሆነ “ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ጠንከር ያሉ ምላሾችን እንደምትሰጥ” አርብ ዕለት አስፈራርታለች፡፡ አሜሪካን ጨምሮ የደቡብ ኮሪያ አጋሮች በቀጠናው ውጥረቱ እንዲፈጠር አድርገዋል በማለት ሰሜን ኮሪያ እየከሰሰች ነው፡፡
የሰሜን ኮሪያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኬሲኤንኤ በሰጠው መግለጫ በአሜሪካ ተጽእኖ ስር ያለው የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት በፒዮንግያንግ ላይ ጫና ማሳደሩን የሚቀጥል ከሆነ ተጨማሪ ወታደራዊ እርምጃ እንደሚወስድ ገልጻለች፡፡
ይህ መግለጫ የወጣው ደቡብ ኮሪያ እና አሜሪካ እየጨመረ የመጣውን የሰሜን ኮሪያ የኒውክሌር እና የሚሳኤል ስጋትን በተሻለ ሁኔታ ለመከላከል በሚደረገው ጥረት ለዓመታዊ ወታደራዊ ልምምዶች እየተዘጋጁ ባሉበት ወቅት ነው።
አጋሮቹ የአሜሪካን የኒውክሌር ንብረቶችን ስራዎች ለማሻሻል እና መደበኛ የፀደይ ወቅት የፍሪደም ጋሻ ልምምዶችን በሚቀጥለው ሳምንት በዋሽንግተን ውስጥ በሚቀጥለው ወር ደግሞ በደቡብ ኮሪያ እንደሚያደርጉ የሴኡል መከላከያ ሚኒስቴር አርብ ዕለት አስታውቋል።
ውጥረት ውስጥ የሚገኙት ሰሜን ኮሪያ እና ደቡብ ኮሪያ በወታደራዊ ልምምድ እና የኑክሌር ሙከራ በማድረግ እርስበእርሳቸው ይካተሳሉ፡፡