ፒዮንግያንግ በቅርቡ ሚሳይሎችን ማስወንጨፍ የሚችል አዲስ ሰርጓጅ መርከብ ታሰማራለች ተብሏል
የተባበሩት መንግስታት ድርጅትና ጎረቤት ሀገራት የኒውክሌር መርሀ-ግብሯን እንድታቆም የሚያቀርቡትን ጥሪ የማትቀበለው ሰሜን ኮሪያ፤ መሳሪያውን ለጠላቶቿ ጠንካራ ጋሻ አድርጋ ትመለከታለች።
ብሉምበርግ የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን "የኮሪያን ልሳነ ምድር ሙሉ በሙሉ ከኒውክሌር ነጻ ማድረግ" የሚል ዓላማ ከሰነቀው ከ2018ቱ ስምምነት በኋላ ከአሜሪካ ጋር ድርድር ለመቀጠል ምንም ፍላጎት የላቸውም ብሏል።
ሰሜን ኮሪያ በዚህ ዓመት ከፍተኛ ቁጥር ያለው የሚሳይል ሙከራ ያደረገች ሲሆን የጦር መሳሪያዋን በማሳደግ ላይ ናት ተብሏል።
በቅርቡም በአምስት ዓመታት ውስጥ የመጀመሪያውን የአቶሚክ ቦምብ ሙከራ እንደምታደርግ ይጠበቃል።
1. የኪም ወቅታዊ መርሀ-ግብሮች ምንድን ናቸው?
ሰሜን ኮሪያ የኒውክሌር ጦርን ለመሸከም የተነደፉትን የተለያዩ የባላስቲክ ሚሳይሎችን እያለማች ነው። ሚሳይሎቹ የአሜሪካ አጋሮችን ደቡብ ኮሪያንና ጃፓንን ለመምታት እንዲሁም የአሜሪካን የጦር ሰፈሮች ሊያጠቁ የሚችሉ የረዥም ርቀት መሳሪያዎች ናቸው።
ፒዮንግያንግ ኒው ዮርክን ወይም ዋሽንግተንን መምታት የሚችሉ አህጉር አቀፍ ባሊስቲክ ሚሳኤሎችንም እየሰራች ነው።
ሰሜን ኮሪያ ከፈረንጆቹ ግንቦት 2019 ጀምሮ ከ80 በላይ የሚሳይል ሙከራዎችን አድርጋለች።
2. ኪም በእርግጥ አሜሪካን ኢላማ ማድረግ ይችሉ ይሆን?
ሀዋሶንግ-17 የተባለው አዲስ እና ትልቅ ሚሳይል በጥቅምት 2020 የሰራተኞች ፓርቲ 75ኛ ዓመት በዓል በወታደራዊ ሰልፍ ላይ ታይቷል።
የነዳጅ ቴክኖሎጂን የሚጠቀም አህጉር አቋራጭ ባሊስቲክ ሚሳይል በማምረት ላይ የምትገኝ ሲሆን፤ አሜሪካ መተኮሱን እንዳታውቅ የሚያደርግ ቴክኖሎጂ አለው ነው የተባለው።
3. ሰሜን ኮሪያ ስንት የኒውክሌር ቦንብ አላት?
ባለሙያዎች እንደሚገምቱት ሰሜን ኮሪያ ከ40 እስከ 50 የሚደርሱ የኒውክሌር ጦር (ራስ) አላት።
በ2021 ሀገሪቱ ስድስት የኒውክሌር ሙከራዎችን አድርጋለች። አሜሪካ፣ ጃፓን እና ደቡብ ኮሪያ ፒዮንግያንግ በቅርቡ ሌላ ሙከራ ታደርጋለች ብለው ይጠብቃሉ።
4. የኪም የጦር ቁሳቁሶችን ከየት ያመጣሉ?
ለብዙ አስርተ ዓመታት ፒዮንግያንግ የኒውክሌር ጦር መሳሪያዎችን ማምረት የሚያስችላትን ዋናነኛ ንጥር "ፋይሲል" ቁሳቁስ ራሷን ችላለች።
ዛሬ መርሀ-ግብሩ በበለጸገ ዩራኒየም ላይ የተመሰረተ ሲሆን፤ ባለሙያዎች እንደሚናገሩት መርሀ-ግብሩ በየዓመቱ ስድስት ቦምቦችን ማምረት የሚያስችለውን ቁሳቁስ ያመርታል።
5. ለኪም ሌላ ለምን እየተዘጋጁ ነው?
ሰሜን ኮሪያ በርካታ የጦር ራሶችን መሸከም የሚችሉ እና የአየር መከላከያዎችን ማምለጥ የሚችሉ አህጉር አቀፍ ባለስቲክ ሚሳኤሎችን ታመርታለች ተብሎ ይጠበቃል።
ኪም የባህር ሰርጓጅ መርከቦችን ለመስራት ጥረት አድርገዋል የተባለም ሲሆን፤ በቅርቡ አዲስ ሰርጓጅ መርከብ ለማሰማራት በጉጉት እየተጠባበቁ ነው ተብሏል። ይህም ሚሳይሎችን ማስወንጨፍ እንደሚችል ባለሙያዎች ይናገራሉ።
6. ሀገሪቱ የመሳሪያ ልማቱን ወጪ እንዴት ቻለችው?
እንደ አሜሪካ የመከላከያ መረጃ ኤጀንሲ ግምገማ ሰሜን ኮሪያ በዓመት ከ7 እስከ 11 ቢሊዮን ዶላር ታወጣለች። ይህም ማለት ሀገሪቱ ለጦር ኃይሏ የምጣኔ-ሀብቷ ከ20 እስከ 30 በመቶ የሚሆነውን ታወጣለች።
የተጣለባት ዓለም አቀፋዊ ማዕቀብ ጉዳት ቢያደርስባትም ሰሜን ኮሪያ የታገዱ ምርቶቿን በድብቅ ትሸጣለች ተብሏል።
የኪም አገዛዝ በሳይበር ወንጀል ወደ 2 ነጥብ 3 ቢሊዮን ዶላር ገደማ አከማችቷል ተብሎም ይታመናል።