ኪም ጆንግ ኡን ከህዝብ እይታ ሲጠፉ ይህ ለሶስተኛ ጊዜ መሆኑ ነው
የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንጉ ኡን ከአደባባ እይታ መጥፋት በርካቶችን እያነጋገረ ያለው ጉዳይ ሆኗል፡፡
የእንግሊዙ ጋዜጣ “ደይሊ ሜይል” ይዞት የወጣ መረጃ እንደሚያመለክተው ከሆነ “ ኪም ላለፉት 35 ቀናት ከህዝብ እይታ ጠፍተዋል” ብለዋል፡፡
አሜሪካ በኮሪያ ልሳነ ምድር “ቀይ መስመሩን እያለፈች ነው”- ሰሜን ኮሪያ
የኪም መጥፋት ስለ የጤና መታወክና ቀጣይ ተተኪ እንዲወራ በሪ ከፍቷልም ነው የተባለው፡፡
በተለይም ፕሬዝዳንቱ የፓርቲያቸው ፖሊት ቢሮ ባካሄደውና በግብርና ጉዳዮች ላይ በመከረው ስብሰባ ላይ አለመታየታቸው ደግሞ ኪም ምናልባትም “የጤና ችግር” ገጥሟቸው ሊሆን ይችላል የሚል ወሬ በስፋት እንዲነዛ ምክንያት ሆኗል፡፡
መንግስት ሚዲያ ድረ-ገጽ እንደሚለው ግን የኪም መጥፋት ኪዘህ ቀደም ከነበሩት የተለየ አይደለም፡፡
ኪም ከህዝብ እይታ ሲጠፉ ይህ ለሶስተኛ ጊዜ መሆኑ ነው፡፡ ባለፈው አመት በሰኔ እና መስከረም በተደረጉ ስብሰባዎች ሳይታዩ መቅረታቸው ሚታወስ ነው፡፡
ሆኖም አሁን ጥያቄው ኪም ጆንግ ኡን ፒዮንጊያንግ በቅርቡ በምትካብረው የሰሜን ኮሪያ ጦር 75ኛ አመት የምስረታ በዓል ላይ ይገኛሉ ወይስ አይገኙም የሚል ሆኗል፡፡
መቀመጫውን አሜሪካ ያደረገው “38 ኖርዝ” የሳተላይት ምስሎች እንደሚያሳዩት ፤ የኮሪያ ህዝብ ጦር የምስረታ በአል ለማክበር ከጥር ወር ጀምሮ ዝግጅት እየተደረገ ነው፡፡
ምስሎቹ ወታደራዊ አውሮፕላኖች በማዕከላዊ ፒዮንግያንግ ላይ በምሽት ዝቅ ብለው ሲበሩም ያሳያሉ፡፡
ለከፍተኛ የምግብ እጥረት የተጋለጠችው ሰሜን ኮሪያ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ህዝባዊ ስነ ስርአቶችን የምታካሂደው ምሽት በጨለማ ውስጥ ነው፡፡
ከሰሞኑ ወታደራዊ ትጥቆቿን በታላቅ ድምቀት በቴሌቭዥን ስታቀርብ እንደነበርም ይታወሳል፡፡