ጃፓን ከ500 በላው ቶምሀውክ ሚሳኤሎችን የመግዛት እቅድ እንዳላት አስታውቃለች
ጃፓን ሰሜን ኮሪያ በመስጋት አሜሪካ ሰራሽ ሚሳኤል ልትታጠቅ መሆኗን ገለጸች።
ሰሜን ኮሪያ በተደጋጋሚ የምታደርጋቸው የኑክሌር ጦር መሳሪያ ሙከራዎች የእስያ ፓስፊክ እና አሜሪካ ሀገራትን አስፈርቷል።
ይህን ተከትሎም የአካባቢው ሀገራት ራሳቸውን ከሰሜን ኮሪያ ሊሰነዘር የሚችል የሚሳኤል ጥቃትን ለመከላከል የጦር መሳሪያ ሸመታ ላይ ናቸው።
- ጃፓን በፈረንጆቹ 2030ዎቹ ሦስት ሽህ ኪሎ ሜትር የሚምዘገዘጉ ሚሳይሎችን ልታለማ ነው
- ጃፓን ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ ትልቁን ወታደራዊ ግንባታ ይፋ አደረገች
ጃፓን ከነዚህ ሀገራት መካከል አንዷ ስትሆን ቶምሀውክ እና ሀይፐርሶኒክ ሚሳኤል የተሰኙት አሜሪካ ሰራሽ ዘመናዊ የጦር መሳሪያን የመግዛት እቅድ እንዳላት ገልጻለች።
እነዚህ ሁለቱ የጦር መሳሪያዎች ከሰሜን ኮሪያ በባህር እና አየር ላይ ሊሰነዘሩ የሚችሉ ጥቃቶችን ለመመከት እንደምታውለው አስታውቃለች።
እንደ ጃፓኑ ሳንኬ ጋዜጣ ዘገባ ከሆነ ጃፓን 500 ቶምሀውክ ሚሳኤል የመግዛት እቅድ ይዛለች።
የቶምሀውክ ሚሳኤል አንዱ ምርት 1 ነጥብ 4 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣ ሲሆን ከ1 ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ ርቀት ያለ ኢላማን የመምታት አቅም አለው ተብሏል።
ሌላኛው ጃፓን ልትታጠቀው የምትፈፋገው ጦር መሳሪያ የረጅም ርቀት ተጓዥ ሀይፐር ሶኒክ ሚሳኤል ሲሆን ይህ የጦር መሳሪያ እስከ 2ሺህ 700 ኪሎ ሜትር ድረስ የመጓዝ አቅም እንዳለው ተገልጿል።