ዝነኛው የቼዝ ተጨዋች ከለበሰው ጅንስ ጋር በተያያዝ በተነሳ አለመግባባት ከውድድር ወጣ
ፌደሬሽኑ የአለባበስ መመሪያው የተዘጋጀው "ሙያዊነትን እና ለሁሉም ተሳታፊዎች ኢፍትሃዊነት ለማረጋገጥ ነው" ብሏል
የለበሰውን ጅንስ ሱሪ ለመቀየር ፍቃደኛ አለመሆኑን የገለጸው እውቁ የቼዝ ተጨዋች ማግኑስ ካርልሰን ከኒው ዮርኩ አለምአቀፍ ውድድር ትቶ መውጣቱ ተዘግቧል
ዝነኛው የቼዝ ተጨዋች ከለበሰው ጅንስ ጋር በተያያዝ በተነሳ አለመግባባት ከውድድር ወጣ።
የለበሰውን ጅንስ ሱሪ ለመቀየር ፍቃደኛ አለመሆኑን የገለጸው እውቁ የቼዝ ተጨዋች ማግኑስ ካርልሰን በኒው ዮርክ እየተካሄ የሚገኘውን 'ወርልድ ራፒድ ኤንድ ብሊትዝ' የተባለውን አለምአቀፍ ውድድር ትቶ መውጣቱ ተዘግቧል።
አለምአቀፉ የቼዝ የፌደሬሽን ባለፈው አርብ እለት እንደገለጸው መመሪያዎቹ ተሳታፊዎች በውድድር ወቅት ጅንስ እንዳይለብሱ የሚከለከለውን ድሬስ ኮድን ወይም የአለባበስ መመሪያን ያካትታሉ።
"ዋና ዳኛው ካርልሰን ህግ መጣሱን አሳውቆት 192 ዶላር ቅጣት ከጻፈበት በኋላ የለበሰውን ጅንስ እንዲቀይር ነግሮታል" ሲል ፌደሬሽኑ በጽረ- ገጹ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
"ነገርግን ካርልሰን ፍቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል። በዚህ ምክንያት በዘጠነኛው ዙር መሳተፍ አልቻለም። ይህ ውሳኔ ያለአድልዎ የተላለፈ እና ለሁሉም በተጨዋቾች በእኩልነት የሚተገበር ነው።"
የ 34 አመቱ ኖርዌጂያን የቼዝ አለቃ በኤክስ ገጹ ባስተላለፈው የቪዲዮ መልእክት የተጣለበትን 192 ዶላር ቅጣት መቀበሉን ገልጿል። ነገርግን የኒው ዮርኩን ውድድር ከማቋረጡ በፊት ሱሪውን ለመቀየር ፍቃደኛ አልነበረም።
"እኔ ያልኩት ግዴታ ከሆነ 'ነገ እቀይራለሁ' ነው ያልኩት" ብሏል በቪዲዮ መልእክቱ። "ነገርግን አሁን መቀየር አለብህ አለኝ፤ በዚያ ሰአት ለእኔ የአቋም ጉዳይ ሆኖ ነበር።"
ፌደሬሽኑ የአለባበስ መመሪያው የተዘጋጀው "ሙያዊነትን እና ለሁሉም ተሳታፊዎች ኢፍትሃዊነት ለማረጋገጥ ነው" ብሏል።
የአለባበስ መመሪያ የጣሰ ኢያን ኒፖምኒአቺቺ የተባለ ሌላ ተሳታፊም አርብ እለት ጠዋት መቀጣቱን ገልጿል ፌደሬሽኑ። ነገርግን ሬደሬሽኑ እንደገለጸው ይህ ተጨዋች መመሪያውን አክብሮ ልብሱን ቀይሯል።
ፌደሬሽኑ "እነዚህ ህጎች ለአመታት ተግባራዊ ሲደረጉ የቆዩ፣ ሁሉም ተሳታፊዎች በደንብ የሚያውቋቸው እና ከውድድሩ በፊት የተነገሯቸው ናቸው" ብሏል።