የዩክሬኑ ኦዴሳ ወደብ በሩሲያ ጥቃት ጉዳት ደረሰበት
የዩክሬን አየር ኃይል በምሽት የተተኮሱ ስድስት ሚሳይሎችና ከ36 ድሮኖች 31ዱን መትቶ መጣሉን አስታውቋል
አብዛኛዎቹ ወደቦቿ በሩሲያ የተያዙባት ዩክሬን በመርከብ ስንዴ ወደ ውጭ ለመላክ የምትጠቀምበት ይህን ወደብ ነበር
የዩክሬኑ ኦዴሳ ወደብ በሩሲያ የአየር ጥቃት መውደሙ ተገልጿል።
የዩክሬን ባለስልጣናት እንደተናገሩት ትናንት ምሽት ሩሲያ ባደረሰችው የአየር እና የሚሳይል ጥቃት ዋነኛ የእህል መጫኛ የሆነው ኦደሳ ወደብ የሚገኝ መሰረተ ልማት መውደሙን ሮይተርስ ዘግቧል።
ኦደሳ ላይ ጥቃት የደረሰው ሩሲያ እና ክሪሚያን የሚያገናኘው ድልድይ በዩክሬን ጥቃት ደርሶበታል ያለችው ሩሲያ አጸፋ እንደምትመልስ መግለጿን ተከትሎ ነው።
የዩክሬን አየር ኃይል እንደገለጸው በምሽት የተኮሱ ስድስት ሚሳይሎች እና ከ36 ድሮኖች 31ዱን መትቶ መጣሉን አስታውቋል።
ሚሳይሉና አብዛኞቹ ድሮኖች በኦደሳ እና ማይኮላይቭ የተመቱ ሲሆን ቀሪዎቹ ደግሞ በምስራቃዊ ግዛቶች ወድቀዋል ተብሏል።
የዩክሬን ደቡብ እዝ እንደገለጸው የድሮን ስብርባሪዎች በወደቡ መሰረተ ልማት ላይ ጉዳት ማድረሱን ተናግሯል።
አብዛኛዎቹ ወደቦቿ በሩሲያ የተያዙባት ዩክሬን በመርከብ ስንዴ ወደ ውጭ ለመላክ የምትጠቀምበት ይህን ወደብ ነበር
ሩሲያ በትናንትናው እለት ከጥቁር ባህር የእህል ስምምነት መውጣቷ ዩክሬን እህል ወደ ውጭ እንዳይወጣ እንቅፋት ይሆናል ተብሏል።
ሩሲያ ከስምምነቱ የወጣችው ስምምነቱ እንዲራዘም ሩሲያ ያስቀመጠችው ቅድመ ሁኔታ ባለመሟላቱ መሆኑን ገልጻለች።