የዩክሬን ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ የሶስተኛው የዓለም ጦርነት ፍርሃት 'ምክንያታዊ' ነው አሉ
ዩክሬን ከሩሲያ ጋር እየተዋጋች የኔቶ አባል መሆን አትችልም ተብሏል
ዘለንስኪ ኔቶን መቀላቀል በሚልከው መልዕክት ምክንያት አሁንም ተገቢ እንደሆነ ተናግረዋል
የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ሀገራቸው ከሩሲያ ጋር ጦርነት ላይ እያለች ኔቶ የአባልነት ጥያቄን መቀበል ሦስተኛውን የዓለም ጦርነትን የመቀስቀስ ስጋቱ 'ምክንያታዊ' ነው አሉ።
ፕሬዝዳንቱ ይህን ያሉት የዩክሬን አባልነት ጥያቄ አዎንታዊ ምላሽ ባለማግኘቱ ጥምረቱን ከነቀፉ ከአንድ ቀን በኋላ ነው።
ዘለንስኪ ከኔቶ ዋና ጸሃፊ ጄንስ ስቶልተንበርግ ጋር በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ጥምረቱን መቀላቀል በሚልከው "ምልክት" ምክንያት አሁንም ተገቢ እንደሆነ ተከራክረዋል።
- ቻይና በሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት ከሞስኮ ጋር ከወገነች 3ኛው የዓለም ጦርነት ይነሳል ሲሉ ዘለንስኪ አስጠነቀቁ
- ዩክሬን ኔቶን የምትቀላቀል ከሆነ 3ኛው የዓለም ጦርነት ይነሳል ሲሉ የሩሲያ ባለስልጣን አስጠነቀቁ
"አንድ ሰው ስለ አባልነታችን መናገር እንደሚፈራው አሁን ተረድተናል። ምክንያቱም ማንም የዓለም ጦርነት ለማካሄድ ፈቃደኛ ባለመሆኑ ምክንያታዊ እና ለመረዳት የሚያስቸግር ነው" ብለዋል።
"ዩክሬን እየተዋጋች ነው፤ እናም ጦርነቱ በግዛታችን ላይ እስከቀጠለ ድረስ ዩክሬን የኔቶ አባል ሀገር መሆን እንደማትችል በትክክል ተረድታለች" በማለት አክለዋል።
ነገር ግን የዩክሬን መሪ አክለው "መልዕክቶቾ አስፈላጊ ናቸው" ሲሉ የአውሮፓ ህብረት እጩነታቸውን በማሳያነት አንስተዋል።
የኔቶ መመስረቻ አንቀጽ አምስት ሁሉንም አባል ሀገራት አንድ መከላከያ ናቸው ይላል። ይህ ድንጋጌ ከ9/11 ጥቃት በኋላ አንድ ጊዜ ብቻ ተተግብሯል።