የዓለም ነዳጅ ዋጋ በበርሜል የአራት ዶላር ቅናሽ አሳየ
አንድ በርሜል በ70 ዶላር እየተሸጠ ሲሆን ይህም ከዘጠን ወራት በኋላ የታየ ቅናሽ ሆኖ ተመዝግቧል
የአሜሪካ እና ቻይናን ጨምሮ የዓለም ኢኮኖሚ መቀዛቀዝ ለነዳጅ ዋጋ መቀነስ ትልቁ ምክንያት ነው ተብሏል
የዓለም ነዳጅ ዋጋ በበርሜል የአራት ዶላር ቅናሽ አሳየ፡፡
የዓለማችን ቁጥር አንድ ነዳጅ ሸማች ሀገር የሆነችው ቻይና እና ሌሎች የበለጸጉ ሀገራት ከሰሞኑ የነዳጅ ፍላጎታቸውን ገታ አድርገዋል፡፡
ይህን ተከትሎም የአንድ በርሜል ነዳጅ ዋጋ ከነበረበት 74 ዶላር ወደ 70 ዶላር ዝቅ ያለ ሲሆን ይህም በዘጠኝ ወራት ውስጥ የታየው ትልቁ ቅናሽ ሆኗል፡፡
እንደ ዩሮ ኒውስ ቻይና እና አሜሪካ የነዳጅ ፍላጎታቸውን የቀነሱ ሲሆን በርካታ ሌሎች የዓለማችን ሀገራትም የኢኮኖሚ መቀዛቀዝ አጋጥሟቸዋል፡፡
ይህን ተከትሎም የዓለም ነዳጅ ፍላጎት እስከ 20 በመቶ ቅናሽ ሊያሳይ እንደሚችል የተገለጸ ሲሆን በነሀሴ ወር ውስጥ በመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት የነበሩ ውጥረቶች የነዳጅ ዋጋ እንዲጨምር አድርገው ነበር፡፡
በምህጻረ ቃሉ ኦፔክ ፕላስ የሚባለው የዓለም ነዳጅ አምራች እና ላኪ ሀገራት ባሳለፍነው ሐምሌ ወር ላይ ዕለታዊ የነዳጅ ምርት መጠን እስከ 2025 የመጨረሻው ወራት ድረስ በ3 ነጥብ 6 ሚሊዮን በርሜል እንዲቀንስ ውሳኔ አስተላፎ ነበር፡፡
ደቡብ ሱዳን በኢትዮጵያ በኩል የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ለመገንባት ከቻይና ጋር ተስማማች
ይሁንና በመካከለኛው ምስራቅ ውጥረቶች በመኖራቸው፣ በሊቢያ ነዳጅ መመረት በመቆሙ እና በሌሎች ምክንያቶች የነዳጅ ምርት እጥረት እንዳያጋጥም በሚል በየዕለቱ ተጨማሪ 180 ሺህ በርሜል ነዳጅ እንዲመረት ተስማምተዋል ተብሏል፡፡
ይህ ሁሉ በሆነበት ሁኔታ የዓለም ነዳጅ ዋጋ ቅናሽ ማሳየቱ አግራሞትን የፈጠረ ሲሆን የስራ መቀዛቀዝ በመላው ዓለም እንዲያጋጥም ማድረጉ ተገልጿል፡፡
የዓለም ነዳጅ ዋጋ መቀነሱ በዚሁ ከቀጠለም ኦፔክ ከጥቅምት ወር ጀምሮ በየዕለቱ 180 ሺህ በርሜል ነዳጅ ተጨማሪነት እንዲመረት ያስተላለፈውን ውሳኔ ሊሽር እንደሚችል አስታውቋል፡፡