ለሳይበር ጥቃቶች መጨመር ምክንያት ከሆኑ ጉዳዮች መካከል አንዱ ኮቪድ-19 ነው ተባለ
ባለፉት 6 ወራት ብቻ የጥቃት መጠኑ ከአምስት እጥፍ በላይ መጨመሩንም ጥናቱ ጠቁሟል
በፋይናንስ ተቋማት ላይ የሚሰነዘረው የሳይበር ጥቃት በ5 እጥፍ መጨመሩን ጥናት አመልክቷል
በፋይናንስ ተቋማት ላይ የሚሰነዘረው የሳይበር ጥቃት በ5 እጥፍ መጨመሩን ጥናት አመልክቷል
በዓለም አቀፍ ደረጃ በፋይናንስ ተቋማት ላይ የሚሰነዘረዉ የሳይበር ጥቃት በ 5 እጥፍ መጨመሩ ጥናት አመለከተ፡፡
የፈረንጆቹ 2020 ከገባ በኋላ በነበሩት ጥቂት ወራት በዓለም አቀፍ ደረጃ በፋይናንስ ተቋማት ላይ የሚሰነዘረዉ የሳይበር ጥቃት በ 5 እጥፍ መጨመሩን አርክቲክወልቭ የ2020 ዓመታዊ የደህንነት ኦፕሬሽን ሪፖርቱ ላይ ገልጿል፡፡
የቅድመ ሳይበር ጥቃት መለያ ምርቶች አቅራቢ ኩባንያዉ "አርክቲክወልቭ" የፊሺንግ /phishing/ እና ራንሰምዌር /ransomware/ ጥቃት በስፋት እየተስተዋለባቸው ከሚገኙ ዘርፎች መካከል የፋይናንስ ዘርፍ ቀዳሚ መሆኑን ያስቀመጠው የኩባንያዉ ጥናት ባለፉት ስድስት ወራት ብቻ የጥቃት መጠኑ ከአምስት እጥፍ በላይ መጨመሩን (520%) ጠቁሟል፡
በፈረንጆቹ አቆጣጠር በ2020 የ2ኛዉ ሩብ ዓመት የተሰነዘረው የፊሺንግ እና ራንሰምዌር ጥቃት ሙከራ ከመጀመሪያዉ ሩብ ዓመት ጋር ሲነጻጸር በ 64 በመቶ መጨመሩን ጥናቱ አሰፍሯል፡፡
ጥናቱ እንደሚለው ለፊሺንግ እና ራንሰምዌር ጥቃት መጨመር ምክንያት ከሆኑት መካከል ኮቪድ-19 አንዱ ሲሆን የመረጃ መንታፊዎችም ኮቪድ-19ኝን እንደ ርዕስ ጉዳይ በመውሰድ ለማጭበርበሪያነት እንደሚጠቀሙበት ተነግሯል፡፡
የኮሮና ቫይረስ በሽታ መከሰቱን ተከትሎ ለደህንነት ክፍተቶች የሚሆኑ መጠገኛዎች (patch) የማቅረቢያ ጊዜም በየ40 ቀኑ እንዲሆን ማድረጉንም ሪፖርቱ አመልክቷል፡፡
ሌላውና ዋናውና የደህንነት ስጋት የሆነው በኮቪድ መከሰቱን ተከትሎ ስራን በቤት ውስጥ ሆኖ መስራት በመጀመሩ ሳቢያ ደህንነቱ ባልተጠበቀ የWi-Fi አጠቃቀም በ240 በመቶ የሳይበር ጥቃት ጭማሪ ማሳየቱ እንደሆነ ሪፖርቱ ጠቁሟል፡፡
ከዚህ ባሻገር በዳርክ-ዌብ (dark web) ላይ በስውር መቀመጥ የነበረባቸው የኮርፖሬት ሚስጥራዊ የይለፍ-ቃሎች በግላጭ የመታየት መጠናቸው ከአራት እጥፍ በላይ (429%) ማሻቀቡን ኩባንያዉ ይፋ አድርጓል
በየአመቱ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ፣ ቴክኖሎጂ ምርት ሻጮች እና የደህንነት መፍትሄዎች ይወጣሉ፡፡ ሆኖም ይህ የማያቋርጥ አዳዲስ የቴክኖሎጂ ፈጠራ ቢኖርም የሳይበር ጥቃት ክስተቶች የዜና ርዕሰ ጉዳይ ከመሆን አልወጡም ሲል ኢንፎሴክ ማጋዚን በድረ-ገጹ አስነብቧል፡፡
የራንሰምዌር ጥቃቶች ፣ የአካዉንት ላይ የሚፈጸሙ ጠለፋዎች እና በሚስጥራዊ የመረጃ ማከማቻ ላይ የሚፈጠርን መፋለስ ለመፍታት ብቸኛው መንገድ ተጠቃሚ ሰዎችን የአተገባባር ሂደቶችን እና ቴክኖሎጂን ሙሉ በሙሉ የሚያቀናጁ የደህንነት ስራዎችንና አቅሞችን መተግበር ይጠይቃል፡፡
የአርክቲክወልቭ የደህንነት አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት የሆኑት ማርክ ማንግሊክሞት በበኩላቸዉ “የሳይበር ደህንነት ኢንዱስትሪው የውጤታማነት ችግር አለበት ሲሉ አስተያየት ስለመ ስጠታቸው ከኢትዮጵያ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ (ኢንሳ) የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡