ዶ/ር ርያን “በሽታው እየተስፋፋ ነው፤ ወደ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እየሄድን ነው”ሲሉ አስጠንቅቀዋል
ዶ/ር ርያን “በሽታው እየተስፋፋ ነው፤ ወደ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እየሄድን ነው”ሲሉ አስጠንቅቀዋል
የዓለም ጤና ድርጅት የተቀመጠው “ምርጥ ግምት” እንደሚያመለክተው በዓለም ደረጃ ከ10 ሰዎች አንዱ በኮሮና ቫይረስ ሳይያዝ እንደማይቀር ነው ብሏል፡፡
ይህን አስተያየት የሰጡት የድርጅቱ የድንገተኛ ዘመቻ ኃላፊ ዶክተር ሚካኤል ርያን 34ኛውን አስፈፃሚ ስብሰባ ላይ ንግግር ባደረዱበት ወቅት ነው፡፡ቁጥሮቹ ከከተማ ወደ ገጠር አንዲሁም በተለያዩ ቡድኖች መካከል ቢለያዩም አብዛኛው የዓለም ክፍል አደጋ ውስጥ መሆኑን አንስተዋል፡፡
“በሽታው እየተስፋፋ ነው፤ ወደ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እየሄድን ነው”ሲሉ አስጠንቅቀዋል፡፡
የድርጅቱ ኃላፊ ዶ/ር ቴድርስ አድሃኖም የዶ/ር ርያንን ሀሳብ አጠናክረው፣ በበሽታው ምክንያት ህይወታቸውን ላጡ ሰዎች የህሊና ጸሎት አድርገዋል፡፡
ርያን እንደገለጹት ደቡባዊ ኢሲያና ቫይረሱ እየተስፋፋ ሲሆን በአውሮፓና በምስራቅ ሜዲትራኒያን የሞት ቁጥር ጨምራል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በአፍሪካና ምእራብ ፓስፊክ እየተሻሻለ መምጣቱን ተናግረዋል፡፡
ህንድ በአሁኑ ሰአት ከፍተኛ መጠን በሚያዙ ሰዎች ቁጥር ቀዳሚ ሆናለች፤ ባለፉት 24 ሰአታት ብቻ 60ሺ የሚሆኑ ሰዎች በየቀኑ እየተያዙ ይገኛሉ፡፡ በህንድ ከሁለት ቀናት በፊት100ሺ በቫይረሱ ምክንያት ሞተዋል፡፡
ርያን እንደገለጹት ምንም እንኳን ቫይረሱ እየተስፋፋ ቢሆንም ስርጭቱን የምንቀንስበት እድል መኖሩን ተናግረዋል፡፡