“ኦፕንሃይመር” የምርጥ ፊልም ክብረ ወሰን ተቀዳጅቷል
96ኛው አካደሚ ሽልማቶች (ኦስካር ሽልማት) በደመቀ፤ ደግሞም ብዙዎችን ባስገረመ አጋጣሚዎች ተውቦ እሁድ ምሽት ተከናውኗል።
በ2024 የኦስካር ሽልማት ላይ “ኦፕንሃይመር” የተሰኘው የባዮግራፊካል ድራማ ዘውግ ያለው ሲኒማ 7 የአስካር ሽልማቶችን ጠራርጎ በመውሰድ ተወዳዳሪ ያልተገኘት መነጋገሪያ ፊልም መሆን ችሏል።
“ኦፕንሃይመር” ፊለም፤ በዘንድሮው የኦስካር ሽልመት ላይ በ13 ዘርፎች ታጭቶ ነው በሰባት ዘርፎች ማሸነፍ ማቻሉ የተነገረው።
በዚህም መሰረት
ኦፕንሃይመር ፊልም
ምርጥ ፊልም፣ ምርጥ ሲኒማቶግራፊ፣ ምርጥ የማጀመቢያ ሙዚቃና ፣ ምርጥ ይሬክተር ካሸነፈባው ዘርፎች ውስጥ ቀዳሚዎች ናቸው
-ፑር ቲንግስ ፊልም
ምርጥ ፕሮዳክሽን ዲዛይን፣ ምርጥ የፊት ገጽ ቅብና ጸጉር እንዲሁም ምርጥ አልባሳት ዲዛይን
ምርጥ ሴት መሪ ተዋናይት፤ ኤማ ስቶን ምርጥ ወንድ መሪ ተዋናይ፤ ሲሊያን መርፊ ምርጥ ዳጥሬክተር፤ ክሪስቶፈር ኖላን ምርጥ ሴት ረዳት ተዋናይት፤ ዳቪን ጀይ ራንዶልፍ ምርጥ ወንድ ረዳት ተዋናይ፤ ሮበርት ዳዎኔይ ጄ.አር
በምርጥ አጭር አኒሜሽን ፊልም፤ ዋር ኢስ ኦቨር በአኒሜሽን ፊልም፤ ዘ ቦይ ኤንድ ዘ ሄሮን
ምርጥ ኦሪጅል ስክሪንፕሌይ አናቶሚ ኦፍ ፎል በምርጥ የትርጉም ስክሩንፕሌይ አሜሪካን ፊክሽን
ምርጥ ዶኩመንተሪ ፤ 20 ዴይስ ኢን ማሪፑል ምርጥ አጭር ዶኩመንተሪ፤ ዘ ላስት ሪፔይር ሾፕ