የኮቲዲቯር የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊና ተሳታፊዎቹ ምን ያህል ሽልማት ያገኛሉ?
እሁድ ፍጻሜውን በሚያገኘው 34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ሻምፒዮን የሚሆነው ቡድን 7 ሚሊየን ዶላር ያገኛል
ሽልማቱ ሴኔጋል ከሶስት አመት በፊት ዋንጫ ስታነሳ ካገኘችው በ40 በመቶ ብልጫ አለው ተብሏል
በድራማዊ ክስተቶች የታጀበውና ከዋክብቱን በጊዜ ሸኝቶ አዳዲሶቹን ፈርጦች ይዞ የቀጠለው 34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ከቀናት በኋላ ፍጻሜውን ያገኛል።
በነገው እለትም ናይጀሪያን ከደቡብ አፍሪካ፤ አስተናጋጇን ኮቲዲቯር ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንግ የሚያገኙት የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታዎች ተጠባቂ ሆነዋል።
60 ሺህ ተመልካቾችን የሚይዘው አላሳን ኡታራ ስታዲየም የእሁዱን የፍጻሜ ጨዋታ ለማስተናገድ ተዘጋጅቷል።
ከ24 ብሄራዊ ቡድኖች አራት ብቻ የቀሩበት ውድድር ማራኪ ፉክክር ከማስተናገዱ ባሻገር ካሜሮን ካዘጋጀችው 33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ዳጎስ ያለ ሽልማት ይዞ መምጣቱ ተነግሯል።
የኮቲዲቯሩ የአፍሪካ ዋንጫ ምን ያህል ያሸልማል? ከ33ኛው ዋንጫስ ምን ያህል ብልጫ አለው?
1. ሻምፒዮን፦ 7 ሚሊየን ዶላር (የ40 በመቶ ጭማሪ)
ካሜሮን ባስተናገደችው የ2021 የአፍሪካ ዋንጫ ሻምፒዮን የሆነችው ሴኔጋል 5 ሚሊየን ዶላር መሸለሟ ይታወሳል።
2. የፍጻሜው ተሸናፊ (2ኛ) – 4 ሚሊየን ዶላር (የ1 ነጥብ 3 ሚሊየን ዶላር ጭማሪ)
3. የግማሽ ፍጻሜ ተሸናፊዎች (2)- 2.5 ሚሊየን ዶላር (እያንዳንዳቸው)
4. ሩብ ፍጻሜውን የተቀላቀሉ (4)- 1.3 ሚሊየን ዶላር (የ500 ሺህ ዶላር ጭማሪ)
5. በጥሎ ማለፉ የተሰናበቱ (8)- 800 ሺህ ዶላር
6. ከምድባቸው ሶስተኛ ደረጃን ይዘው ወደ ጥሎ ማለፉ ያልተቀላቀሉት (ጋና እና ዛምቢያ) - 700 ሺህ ዶላር
7. በየምድባቸው አራተኛ ሆነው ያጠናቀቁ (6) - 500 ሺህ ዶላር