ለክትባቱ ብቁ ከሆኑ የሃገሪቱ ዜጎች መካከል 65 በመቶ ያህሉ ተከትበዋል ተብሏል
የኮሮና ክትባቶችን ለማግኘት ለተቀመጡ መስፈርቶች ብቁ ከሆኑ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ነዋሪዎች መካከል አብዛኞቹ ክትባቱን ማግኘታቸው ተነገረ፡፡
ከ16 ዓመት በላይ ከሆኑ የሃገሪቱ ነዋሪዎች መካከል 65 በመቶ ያህሉ የኮሮና ክትባቶችን ማግኘታቸው ተነግሯል፡፡
ዩኤኢ እስከ ትናንት ሚያዚያ 20 ቀን 2013 ዓ/ም ድረስ 9 ነጥብ 5 ሚሊዬን ክትባቶችን ሰጥታለች፡፡
ክትባቶች በአንደኛ እና በሁለተኛ ዙሮች የተሰጡ ናቸው፡፡
ለ10 ሚሊዬን እንደጠጋ ከሚነገርለት ህዝቧ መካከል ከ5 ሚሊዬን የሚልቀው የመጀመሪያ ዙር ክትባቶችን አግኝቷል፡፡
4 ሚሊዬን ገደማ ሰዎች ደግሞ ለሁለተኛ ጊዜ ተከትበዋል እንደ ሃገሪቱ ብሔራዊ የድንገተኛ አደጋ እና የአደጋ አስተዳደር ባለሥልጣን ገለጻ፡፡
እንደ ባለስልጣኑ ከሆነም 75 በመቶ ያህሉ ከ60 ዓመት በላይ አዛውንቶች ክትባቱን አግኝተዋል፡፡
ባለፉት 24 ሰዓታት ብቻ 111,176 ክትባቶች ተሰጥተዋል፡፡
ይህም እስካሁን ከ9 ነጥብ 9 ሚሊዬን በላይ ክትባቶች መሰጠታቸውን የሚያሳይ ነው፡፡
የክትባቱ ውጤታማነት በአብዛኛው በመልካም ጎኑ ሊጠቀስ የሚችል ነው፡፡ ክትባቱን ለሁለተኛ ጊዜ ከወሰዱ መካከል ጥቂቶች ብቻም ናቸው በድጋሚ በቫይረሱ የተያዙት፡፡
ባለስልጣኑ ከቫይረሱ ተጠቂዎች ጥቂቶቹ ብቻ ለሆስፒታል የሚያበቃ ጽኑ ህመም መጋለጣቸውን አስታውቋል፡፡
ያልተከተቡ ዜጎችን እንቅስቃሴ ለመገደብ የሚያስችል ጥብቅ የእንቅስቃሴ ገደብ ማስቀመጡንም የሃገሪቱ መንግስት አስታውቋል፡፡
ዛሬ 1,931 በቫይረሱ መያዛቸውን ባረጋገጠችው በዩኤኢ እስካሁን ከግማሽ ሚሊዬን የሚልቁ ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፡፡