የዩኤኢ ምክትል ፕሬዝዳንት እና ጠ/ሚኒስትር የኮቪድ-19 ክትባት ወሰዱ
ከ ሼክ መሐመድ ቢን ራሺድ በተጨማሪ ሌሎች የዩኤኢ ከፍተኛ ባለሥልጣናትም ክትባቱን ወስደዋል
በሶስት ዙር በተካሔዱ ክሊኒካዊ ሙከራዎች ክትባቱ ደህንነቱ የተጠበቀ መሆኑ ተገልጿል
የዩኤኢ ምክትል ፕሬዝዳንት እና ጠ/ሚኒስትር የኮቪድ-19 ክትባት ወሰዱ
የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ምክትል ፕሬዝዳንት ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የዱባይ ገዥ ሼክ መሐመድ ቢን ራሺድ አል ማክቱም የኮቪድ - 19 ክትባት መውሰዳቸውን በትዊተር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡
ምክትል ፕሬዝዳንቱ የኮሮናቫይረስ ክትባት ለማዘጋጀት የሚሰሩ አካላትን በሙሉ አመስግነዋል፡፡
“ዛሬ የኮቪድ -19 ክትባትን ስንወስድ ለሁሉም ሰው ደህንነት እና ትልቅ ጤንነት እንመኛለን ፤ እንዲሁም ክትባቱን በተባበሩት አረብ ኤምሬትቶች ተደራሽ ለማድረግ ያላሰለሰ ጥረት ባደረጉ ቡድኖቻችን እንኮራለን” ብለዋል፡፡
በዩኤኢ እየበለጸገ የሚገኘውን የቻይና ሲኖፋርም ክትባት ከሼክ መሐመድ ቢን ራሺድ በፊት በርካታ የሀገሪቱ ባለስልጣናትም ወስደዋል፡፡
በዩኤኢ በሶስተኛ ደረጃ በተደረገው የክትባቱ ሙከራ 31,000 በጎ ፈቃደኞች ተሳትፈውበታል፡፡ በዚህም ክትባቱ የጎንዮሽ ጉዳት የሌለው መሆኑ ተረጋግጧል ዘናሺናል እንደዘገበው፡፡
ዘ ላንሴት መጽሔት ላይ ባለፈው መስከረም ወር የታተመ አንድ ጥናት ክትባቱ በደረጃ 1 እና 2 ክሊኒካዊ ሙከራዎች ወቅት ደህንነቱ የተጠበቀ መሆኑን እና ክትባቱን የወሰዱ እስከ 80 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ሰዎች ፀረ እንግዳ አካላትን ማምረታቸውን አመልክቷል፡፡