በኒውዝላንድ ያለ አንድ የበቀቀን ዝርያ ከበራሪነት ዝርዝር አእዋፋት ውስጥ ለመሰረዝ በቅቷል ተብሏል
በቀቀን የመጥፋት አደጋ እንደተጋረጠባት ተገለጸ።
የአየር ንብረት ለውጥ የሰው ልጆችን ህይወት በማወሳሰብ ብዙ ጉዳቶችን በናድረስ ላይ መሆኑ ይታወሳል።
በተለይም ተፈጥሮ የራሷን ሚዛን እንዳትጠብቅ በማድረግ ምድር ለሰው ልጆች ህይወት ተስማሚ እንዳትሆን ማድረግ ከጀመረ ቆይቷል።
ኒውዝላንድ በአየር ንብረት ለውጥ ከሚፈተኑ ሀገራት መካከል አንዷ ስትሆን በሀገሪቱ ከሰባተኛው ክፍለዘመን በፊት ጀምሮ ስትኖር የነበረች የበቀቀን ዝርያ የመጥፋት አደጋ ተጋርጦባታል ተብሏል።
ይህች በቀቀን የአየር ንብረት ለውጥ ባደረሰው ጉዳት ምክንያት ዘሯ እንዲጠፋ አደጋ ከመደቀኑ ባለፈ ህይወቷ እንዲወሳሰብ ወደማድረግ ማድረጉ ተገልጿል።
የኒውዝላንድ በቀቀን ዝርያ ከበራሪ እዕዋፋት ምድብ ውስጥ የምትመደብ ቢሆንም በጊዜ ሂደት ግን መብረር የማትችል የአዕዋፍ ዝርያ ወደ መሆን ተቀይራለች ተብሏል።
በቀቀኗ ወደ አለመብረር የተቀየረው በየብስ ላይ እንደልቧ መኖር ትችላለች የተባለ ሲሆን የኒውዝላንድ አብዛኛው ግዛት በውሀ መመሞላቱ በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ያለው አነስተኛ የየብስ ቦታ በየጊዜው በውሀ በመጥለቅለቁ እንደሆነ ተገልጿል።
የኒውዝላንድ መንግስትም በቀቀኗን ከመጥፋት ለመታደግ ብዙ እቅዶችን አውጥቶ እና በጀት አዘጋጅቶ በመስራት ላይ መሆኑን ገልጿል።