ኒውዝላንድ 51 ሙስሊሞችን በገደለው ነጭ ላይ የእድሜ ልክ እስራት አስተላለፈች
በኒውዝላንድ ፍርድቤት የእድሜ ልክ ጽኑ እስራት ሲያስተላልፍ የመጀመሪያ ጊዜ ነው
ዳኛው ታራንት ለፈጸመው አረመኔያዊ ተግባር ቅጣቱ በቂ አይደለም ብለዋል
ዳኛው ታራንት ለፈጸመው አረመኔያዊ ተግባር ቅጣቱ በቂ አይደለም ብለዋል
የኒውዝላንድ ዳኛ በሀገሪቱ ከባድ ግድያ በተባለውና 51 የሙስሊም አማኞችን በገደለው ብሬንተን ታራንት በተባለ የነጭ የበላይነት አራማጅ ላይ በትናንትናው እለት ምህረት የሌለው የእድሜ ልክ ጽኑ እስራት አስተላልፏል፡፡ ለፈጸመው አረመኔያዊ ተግባር ቅጣቱ በቂ አይደለም ተብሏል፡፡
በኒውዝላንድ ፍርድቤት የእድሜ ልክ ጽኑ እስራት ሲያስተላልፍ የመጀመሪያ ጊዜ ነው፡፡የ29 አመቱ አውስትራሊያዊ ታራንት በ51 የግድያ ክስ፣ በ40 የግድያ ሙከራና በክሪስትቸርች በሚገኙ መስጅዶች ላይ በፈረንጆቹ 2019 የሽብር ድርጊት በመፈጸሙና በፌስቡክ በቀጥታ በማስተላለፉ ነው ለእስር የተዳረገው፡፡
የከፍተኛ ፍርድቤት ዳኛ ካሜሩን ማንደር እንደተናገሩት ፍርዱ በቂ አይደለም ብለዋል፡፡
“ወንደልህ በጣም ዘግናኝ ነው፤ ምንምእንኳን እስከምትሞት ብትታሰርም፣ ላጠፋኸው ጥፋት በቂ አይደለም ” በማለት ዳኛው ፍርዱን ሲያስተላልፉ ተናግረዋል፡፡፡ ደኛው “ጉዳዩን እኔ እስከመራሁት ድረስ” ምንም ርህራሄ እንደማይኖራቸው ለታራንት ነግረውታል፡፡
ዳኛው ፍርዱን ከማስተላለፋቸው በፊት ታራንት መናገር የሚፈልገው ነገር እንዳለው ጠይቀውት ነበር፡፡ ግራጫ የእስርቤት ልብስ ለብሶና በጥበቃዎች ታጅቦ የነበረው ታራንት አስተያየት የመስጠት መብት እንዳለው ያውቅ እንደሆነ ሲጠየቅ ጭንቅላቱን ቢነቀንቅም፤ አልተናገረም፡፡
አቃቤ ህግ ቀድም ብሎ ለፍርድቤት እንደተናገረው ታራንት ወራሪ ናቸው በሚላቸው ላይ ፍርሃትን ለማንገስ እንዳሰበና ከፍተኛ ጉዳት እንዲደርስ በጥንቃቄ አቅዶ ነበር፡፡