ዘለንስኪ ከፍተኛ የጸጥታ ባለስልጣንን ከኃላፊነት አባረሩ
ፕሬዝደንቱ ባለፈው ወር ዩክሬን ከሩሲያ ጋር እያደረገች ባለው ጦርነት ቁልፍ ሚና ነበራቸው የተባሉትን ዋና የጦር አዛዧን ከኃላፊነት ማንሳታቸው ይታወሳል
የዩክሬኑ ፕሬዝደንት ዘለንስኪ እያካሄዱት ባለው የአመራር ለውጥ ዘመቻ የብሔራዊ ጸጥታ ምክር ቤት ጸኃፊን አባረዋል
ዘለንስኪ ከፍተኛ የጸጥታ ባለስልጣንን ከኃላፊነት አባረሩ።
የዩክሬኑ ፕሬዝደንት ዘለንስኪ እያካሄዱት ባለው የአመራር ለውጥ ዘመቻ ከትናንት በስትያ የዩክሬንን የብሔራዊ የጸጥታ ምክር ቤት ጸኃፊ ማባረራቸውን እና በእሳቸው ቦታ የውጭ ደህንነት ኤጀንሲ ኃላፊ የነበሩትን መሾማቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
- በሩሲያ ጦር ላይ የበላይነት ለማግኘት ድሮን ቁልፍ እንደሆነ የዩክሬን ጦር ዋና አዛዥ ተናገሩ
- ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ ከሞስኮ ጥቃት ጋር የዩክሬን ስም መነሳቱ እንዳበሳጫቸው ገለጹ
ፕሬዝደንቱ ባለፈው ወር ዩክሬን ከሩሲያ ጋር እያደረገች ባለው ጦርነት ቁልፍ ሚና ነበራቸው የተባሉትን ዋና የጦር አዛዥ ከኃላፊነት ማንሳታቸው ይታወሳል።
የጸጥታ ኃላፊው መባረራቸውን ይፋ ያደረገው የፕሬዝደንቱ ጽረ-ገጹ የተባረሩበትን ምክንያት ግን ግልጽ አላደረገም።
የተሰናበቱት የብሔራዊ ደህንነት እና የመከላከያ ምክርቤት ጸኃፊው ኦሌክሲ ዳኒሎቭ ፕሬዝደንት ዘለንስኪ ስልጣን ከመያዛቸው ከአንድ ወር በፊት ከ2019 ጀምሮ ሲያገለግሉ ቆይተዋል።
ዘለንስኪ ባስተላለፉት የቪዲዮ መልእክት ዳኒሎቭ አዲስ ኃላፊነን እንደሚሰጣቸው ገልጸዋል።
ዘለንስኪ ዳኒሎቭን ያነሱበትን ምክንያት አላብራሩም፤ ነገርግን የብሔራዊ ደህንነታችንን ለመጠበቅ አስተማማኝ የትንበያ አቅም ማሳደግ ያስፈልጋል ብለዋል።
"ዩክሬንን የማጠናከር እና በሁሉም ዘርፎች ያሉ አሰራሮችን የማደስ ሂደት ተጠናክሮ ይቀጥላል" ብለዋል ዘለንስኪ።
ዘለንስኪ በግልጽ የማይታወቁትን የውጭ ደህንነት ኤጀንሲ ኃላፊ የሆኑትን የ51 አመቱን ኦሌክሳንደር ሊቲቪንኮን ምክርቤቱን እንዲመሩት ሹመት ሰጥቸዋል።
ፕሬዝደንት ዘለንስኪ አዲሱ ተሿሚ ዩክሬን የምትፈልገውን የደህንነት እና የጸጥታ ልምድ ያካበቱ ናቸው ብለዋል።
ተጠሪነቱ ለፕሬዝዳንቱ የሆነው ምክርቤቱ የዩክሬንን ከፍተኛ የፖለቲካ፣ የጸጥታ እና የመከላከያ ኃላፊዎች ያካተተ እና የብሔራዊ ደህንነት ጉዳዮችን የሚያስተባብር ነው።
ፕሬዝደንቱ ምክትል የወታደራዊ ስለላ ምክትል ኃላፊ የነበሩትን ኦሌህ ኢቫስቸንኮን የውጭ ደህንነት ኃላፊ አድርገው ሾመዋቸዋል።
የዩክሬን እና ሩሲያ ጦርነት ሁለት አመት ያለፈው ሲሆን ሩሲያ በቅርቡ በምስራቅ ዩክሬን አቭዲቪካን ጨምሮ በርካታ መንደሮችን ተቆጣጠራለች።
ዩክሬን ቦታዎቹን የለቀቀችው የምዕራባውያን ወታደራዊ እርዳታ በፍጥነት ባለመድረሱ እና ወታደሮቿን ከከበባ ለማውጣታ መሆኑን መግለጿ ይታወሳል።