በሩሲያ ጦር ላይ የበላይነት ለማግኘት ድሮን ቁልፍ እንደሆነ የዩክሬን ጦር ዋና አዛዥ ተናገሩ
የዩክሬኑ ፕሬዝደንት ዘለንስኪ ለድሮን ጥቃት ትኩረት በመስጠት ለድሮን ብቻ የሚሆን ኃይል አቋቁመዋል።
አዛዡ በቁጥር ብልጫ ባለው የ"ጠላት ጦር" ላይ የበላይነት ለማግኘት የተሻለ የድሮን ሲስተም አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል
በሩሲያ ጦር ላይ የበላይነት ለማግኘት ድሮን ቁልፍ እንደሆነ የዩክሬን ጦር ዋና አዛዥ ተናገሩ።
የድሮን አጠቃቀምን ማሳደግ ዩክሬን በቁጥር ብልጫ ባለው የሩሲያ ጦር ላይ የበላይነት ለማግኘት ቁልፍ እንደሆነ የዩክሬን ጦር ዋና አዛዥ ኦሌክሳንደር ሲርስኪይ በትናንትናው እለት ተናግረዋል።
"የድሮን ሲስተምን ማሳደግ ቅድሚያ የምሰጠው ነው"ሲሉ ዋና አዛዡ ስርስኪይ በቴሌግራም ገጻቸው ገልጸዋል።
አዛዡ በቁጥር ብልጫ ባለው የ"ጠላት ጦር" ላይ የበላይነት ለማግኘት የተሻለ የድሮን ሲስተም አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል።
ሁለቱ ሀገራት በጦርሜዳ ከመፋለም ይልቅ በድሮን አንደኛቸው የሌላኛቸውን ወታደራዊ ካምፖችን ወደማጥቃት የተሸጋገሩ ይመስላል።
የሩሲያ ጦር የዩክሬንን ጦር በሰው ሀይል እና በመሳሪያ ብዛት የበላይነት ስለያዝ በበርካታ ግንባሮች ቀስ በቀስ ድል እየተቀዳጀ ይገኛል።
ባለፈው እሁድ የተካሄደውን ምርጫ በማሸነፍ ለተጨማሪ ስድስት አመታት በስልጣን እንደሚቆዩ ያረጋገጡት ፑቲን የሞስኮ ኃይሎች በጦር ግንባር የበላይነት መያዛቸውን እና ወደፊት እየገፉ መሆናቸውን ተናግረዋል።
የዩክሬኑ ፕሬዝደንት ዘለንስኪ ለድሮን ጥቃት ትኩረት በመስጠት ለድሮን ብቻ የሚሆን ኃይል አቋቁመዋል።
ወታራዊ ተንታኞች ድሮን የከባድ መሳሪያ ተተኳሽ እና ሌሎች መሳሪያዎች እጥረት ያለባት ዩክሬን የተሻለ ቴክሎኖሎጂ ተጠቅማ የበላይነት እንድይዝ ያስችላታል ይላሉ። ነገርግን የሩሲያም ድሮን ኢንዱስትሪም በማደግ ላይ ይገኛል።
ዩክሬን በቅርቡ በሩሲያ ግዛት ውስጥ በፈጸመችው በርካታ የድሮን ጥቃቶች የነዳጅ ማጣሪያን ጨምሮ በርካታ መሰረተልማቶችን ማጥቃቷን ገልጻለች።
የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት ከተጀመረ ሁለት አመታትን ያስቆጠረ ሲሆን ሩሲያ በምሰራቅ ዩክሬን ወሳኝ የተባለችውን አብዲቪካ ከተማን ጨምሮ በርካታ መንደሮችን መቆጣጠር ችላለች።
ዩክሬን ከእነዚህ ቦታዎች ለቃ የወጣችው የምዕራባውያን ወታራዊ እርዳታ በመዘግየቱ ነው የሚል ምክንያት ማቅረባ ይታወሳል።