የአሳማ ኩላሊት በሰው ልጆች ላይ የመስራት እድሉ ከፍተኛ መሆኑ ተገለጸ
የኒዮርክ ሐኪሞች የአሳማ ኩላሊትን በሰው ላይ ሞክረውት ተስፋ ሰጪ ውጤት እንዳገኙበት ተናግረዋል
በቤተ ሙከራ የበለጸጉ የእንስሳት ሰውነት አካሎች ለሰው ልጆች ተስማሚ ሆነዋል ተብሏል
የአሳማ ኩላሊት በሰው ልጆች ላይ የመስራት እድሉ ከፍተኛ መሆኑ ተገለ።
በኒዮርክ በጭንቅላት ካንሰር ህምም ሕይወቱ ያለፈ አንድ ግለሰብ አካን በ በጎ ፈቃደኛነት ለምርምር መስጠቱን ተከትሎ የሟቹን ኩላሊት በማውጣት የአሳ ማ ኩላሊት ንቅለ ተከላ ተሰርቶለታል።
ይህ የኩላሊት ንቅለ ተከላ እስካሁን ምንም አይነት ችግር አልታየበት የተ ባለ ሲሆን በኩላሊት ህመም ለሚሰቃዩ ህመምተኞች ተስፋ ሆኗል።
የኒዮርክ ዩንቨርሲቲ የቀዶ ሕክምና ክፍል ተመራማሪዎች የአሳማ ኩላሊትን ወደ ሰው ከገጠሙት በኋላ ወዲያውኑ መስራት ጀምሯል ተብሏል።
እንደ ዩሮ ኒውስ ዘገባ ከሆነ የዩንቨርሲቲው ቀዶ ጥገና የህክምና ቡድ የአ ሳማ ኩላሊትን ሕይወቱ ባለፈ ሰው ላይ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ካደረጉ በዊላ ኩ ላሊቱ ስራ ጀምሯል።
ይህ የአሳማ ኩላሊት ወደ ሰው ከተገጠመ ሁለት ወራት ሲሆን እስካሁን ምንም እንከን እንዳልታየበት ተገልጿል።
ይህ የኩላሊት ቀዶ ህክምና እስካሁን ውጤታማ መሆኑን ተከትሎ ዩንቨርቲው በህይወት ወዳሉ በጎ ፈቃደኛ ሰዎች ላይ የመሞከር እቅድ አለኝ ብሏል።
አዲሱ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ውጤታማ መሆኑን ተከትሎም ሳይንቲስቶች የእን ስሳት የሰውነት አካሎች እንዴት የሰው ልጆችን ህይወት ሊታደጉ ይችላ በሚል አዲስ ነገር ፍለጋው ጨምሯል ተብሏል።
የአፍጋኒስታኗ 'ባለአንድ ኩላሊት መንደር' ኑሮን ለመግፋት አካላቸውን የሸጡ አፍጋናውያን መኖሪያ መንደር
ይሁንና ይህ የአሳማ ኩላሊት በሰው ልጅ ላይ ከተተከለ ተጨማሪ ምርምሮ ችን እና ውጤቶችን ማየት እንደሚያስፈልግ ተገልጿል።
እንደ ተመራማሪዎቹ ገለጻ የእንስሳትን የሰውነት አካል በቀጥታ ወደ ሰው ል ጆች ላይ ንቅለ ተከላ ቢደረግ የሰውነታችን ህዋስ አዲስ የተተከለውን አካል የ ሚያጠቃ በመሆኑ የግድ በቤተ ሙከራ የበለጸጉ የእንስሳት አካሎችን መቀም ያ ስፈልጋል ብለዋል።
በአሜሪካ ከ100 ሺህ በላይ ዜጎች የሰውነት አካል ንቅለ ተከላ ሕክምና ለማድረግ በመጠባበቅ ላይ እንደሆኑ በዘገባው ላይ ተጠቅሷል።