በረራ ላይ ሳለ በሸረሪት ተነድፎ አውሮፕላን በድንገት ያሳረፈው አብራሪ
አብራሪው የተነደፈው ከጀርመን ወደ ስፔን እያበረረ በነበረበት ወቅት መሆኑ ተገልጿል

በየካቲት 2022 ደግሞ ማሌዥያ ውስጥ ከዋና ከተማዋ ኳላ ላምፑር ወደ ሳባህ የሀገር ውስጥ በረራ በሚያደርግ አውሮፕላን ላይ ዘንዶ ተገኝቶ ጉድ ተብሎ ነበር
እያበረረ በነበረበት ወቅት ታራንቱላ በተለባለች መርዛማ ሸረሪት የተነደፈው አብራሪ አውሮፕላኑን በድንገት ለማሳረፍ ተገዷል።
አብራሪው የተነደፈው ከጀርመን ወደ ስፔን እያበረረ በነበረበት ወቅት መሆኑን ዘ ጋርዲያን ጋዜጣ ዘግቧል።
እንደጋዜጣው ዘገባ በሸረሪት የተነደፈው አብራሪ ጸረ-መርዝ መድሃኒት እስከሚሰጠው ድረስ የኢቤሪያ አውሮፕላን በረራ ዘግይቶ ነበር ተብሏል።
ይህ የአየር ላይ ድራማዊ ክስተት የተፈጠረው የኢቤሪያ ኤ320 አውሮፕላን ከጀርመን ዱሰልዶርፍ ተነስቶ ወደ ስፔኗ ማድሪድ ከተማ እየበረረ በነበረበት ወቀት መሆኑን ጋዜጣዊ ጠቅሷል።
ሸረሪቷ አውሮፕላኑ በዚህ ሳምንት መጀመሪያ በሞሮኮ ካዛብላንካ ባረፈበት ወቅት ግብታ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል። አውሮፕላኑ በሰፔን ዋና ከተማ ካረፈ በኋላ እስከሚጸዳ ሶስት ሰአት በመዘግየቱ ወደ ጋሊሺያኗ ከተማ ቪጎ የሚሄዱ ተጓዦች እንዲጠብቁ ተደርገዋል።
አብራራው እብጠት የሚያስከትሉ በሽታዎችን ለማከም የሚውለውና ከከባድ አለርጅክ ጋር የተያያዙ እብጠቶችንና ሌሎች ምልክቶችን ለመቀነስ በስፋት ጥቅም ላይ የሚውለው ኡርባሶን ወይም በሳይንሳዊ ስያሜው ሜታይልፕሬዲኒሶሎን የተባለ መድሃኒት ተሰጥቶታል።
ኢቤሪያ አብራሪው ደህና መሆኑንና በጤናው ላይ የከፋ ጉዳት እንደሚያስከትልበት ቢገልጽም ማድሪድ በደረሰበት ወቅት የህክምና እርዳታ መፈለጉ ወይም አለመፈለጉ ግልጽ አይደለም።
ሸረሪት የወጣችበት አውሮፕላን ከካዛብላንካ ተነስቶ ስፔን ለመድረስ ብራሰልዝ፣ ዙሪክና ቶሎዜን ጨምሮ በከተሞች አርፏል። የጋሊያሽያን ጋዜጣ ላ ቮዝ ዲ ጋላሽያ እንደዘገበው ምንም እንኳን አውሮፕላኑ አርብ ሌሊት ቪጎ ከማረፉ በፊት ቢጸዳም የተወሰኑ መንገደኞች ሸረሪት ፈርተው መቀመጫቸውንና መተላፋያውን በተደጋጋሚ ሲፈትሹ ተስተውለዋል።
ባለፈው ህዳር ወር የአውሮፕላን ጥገና ሰራተኞች ኃይል እንዲቋረጥ የሚያደርጉ 130 የሚሆኑ አይጦች ከበው ለመያዝ ጥረት በሚያደርጉበት ጊዜ ከጉድጓዳቸው በማምለጣቸው ለአምስት ቀናት በረራ ቆሞ ነበር። የመንገደኞችን ቦርሳ የሚቆጣጠሩ ሰራተኞች አይጦቹ የነበሩበት ጉድጓድ በመውደሙ ምክንያት 132 የሚሆኑት መሄዳ አጥተው እቃ ማስቀመጫ አካባቢ ሲሯሯጡ እንደነበረ ገልጸዋል።
በየካቲት 2022 ደግሞ ማሌዥያ ውስጥ ከዋና ከተማዋ ኳላ ላምፑር ወደ ሳባህ የሀገር ውስጥ በረራ በሚያደርግ አውሮፕላን ላይ ዘንዶ ተገኝቶ ጉድ ተብሎ ነበር።
ይህን ተከትሎ አውሮፕላኑ አቅጣጫ ቀይሮ በሳራዋክ ግዛት በሚገኘው ኩቺንግ አለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ለማቅናት መገደዱ ይታወሳል። ተሳቢው ዘንዶ አውሮፕላኑ ውስጥ እየተጠማዘዝ ሲሄድ የሚያሳዩ ምስሎች በማህበራዊ ሚዲያ ከተለቀቁ በኋላ ክስተቱ መነጋገሪያ ሆኖም ነበር።
የማሌዥያ አየርመንድ ባወጣው መግለጫ "እንዲህ አይነት ክስተት የፈጠር እድሉ በጣም ጠባብ ነው" የሚል ምላሽ ሰጥቶ ነበር።