የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ትራምፕ በሞስኮ ጉብኝት ሊያደርጉ እንደሚችሉ ገለጹ
የዩክሬን ጦርነት በሳምንታት ውስጥ እንደሚጠናቀቅ ፍንጭ የሰጡት ፕሬዝዳንቱ የሰላም ስምምነቱ ሲፈጸም ወደ ሞስኮ እንደሚያቀኑ ገልጸዋል

የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በዋሽንግተን ባደረጉት ጉብኝት ከትራምፕ ጋር በአውሮፓ የዩክሬን እቅድ ዙሪያ መክረዋል
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሩስያ ሞስኮ ጉብኝት ስምምነት ሲደረስ ጉብኝት ሊያደርጉ እንደሚችሉ ገልጸዋል።
ወደ ሞስኮ በትክክለኛው ሰዓት አቀናለሁ ያሉት ፕሬዝዳንቱ ትክክለኛ ጊዜ የሚሆነው የሩስያ እና ዩክሬን የሚጠናቀቅበት ወቅት እንደሚሆን ተናግረዋል፡፡
ትራምፕ ጦርነቱ በሳምንታት ውስጥ ሊቆም እንደሚችል ገልጸው በሞስኮ እና ኪየቭ መካከል የሰላም ስምምነቱ ከተፈረመ በኋላ በሩስያ ጉብኝት ሊያደርጉ እንደሚችሉ ጠቁመዋል፡፡
ከሰሞኑ በዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮለድሚር ዘለንስኪ ላይ በሰነዘሩት ከፍተኛ ትችት ከአውሮፓ እና ከዩክሬን ከፍተኛ ተቃውሞ የገጠማቸው ፕሬዝዳንቱ ከፈረንዳዩ ፕሬዝዳንት ጋር በትላንትናው ዕለት በዋሽንግተን ተገናኝተዋል፡፡
በነጩ ቤተ መንግስት ከኢማኑኤል ማክሮን ጋር ባደረጉት ውይይት የአውሮፓ የሰላም አስከባሪ ጦር በዩክሬን መሰማራት የሚኖረውን ጠቀሜታ ከማክሮን ማብራርያ ተደርጎላቸዋል፡፡
የአውሮፓውያንን የዩክሬን የሰላም እቅድ ያቀረቡት ማክሮን የአውሮፓ ጦር መሰማራት የሰላም ስምምነቱን ተፈጻሚነት ለማረጋገጥ ያለውን ወሳኝነት ገልጸዋል፡፡
ከዚህ ባለፈም ጦርነቱን ለማስቆም በሚደረገው የሰላም ውይይት ላይ አውሮፓ እና ዩክሬን እንዲሳተፉ ማክሮን አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
ትራምፕ በበኩላቸው “የስምምነቱን ተፈጻሚነት ለማስጠበቅ የአውሮፓ ወታደሮችን ወደ ዩክሬን መላክ ምንም ችግር አይታየኝም” ብለዋል።
ሩሲያ የአውሮፓ ወታደሮች በዩክሬን መሰማራት ለግጭቱ ማብቃት ዋስትና አድርጎ ለመቀበል ዝግጁ መሆኗን ገልጸዋል።
እሳቸው ይህን ቢሉም ባሳለፍነው ሳምንት የአውሮፓ መሪዎች ባደረጉት አስቸኳይ ስብሰባ ተነሳውን የሰላም አስከባሪ ጦር ስምሪት ሉአላዊነትን እንደመጋፋት ነው በሚል ሞስኮ ውድቅ ማድረጓ ይታወሳል፡፡
“አላማየ ዩክሬንን ከዚህ አስከፊ ጦርነት ማውጣት ነው” ያሉት ትራምፕ ከሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በጦርነት ማስቆም ሂደት ዙሪያ ሰፊ ውይይት እና መግባባት ላይ መድረሳቸውን ለማክሮን ነግረዋቸዋል፡፡
አሜሪካ ለዩክሬን የሰጠችው ብድር ለየት ባሉ ማዕድናት እንዲመለስ የጠየቁት ፕሬዝዳንቱ “እንድታውቁት የምፈልገው አውሮፓ ለዩክሬን የሰጠውን ብድር እያስከፈለ ነው ወደ ኋላ የቀረነው እኛ ነን፤ በዚህ ሳምንት ዘለንስኪ ወደ ኋይት ሀውስ መጥቶ ብድሩን በማዕድን ለመመለስ ፊርማ ይፈርማል” ብለዋል፡፡
አውሮፓ እንደ አህጉር እስካሁን ለዩክሬን የሰጠው 100 ቢሊየን ዶላር ሲሆን አሜሪካ ደግሞ በተለያዩ አይነት የድጋፍ ማዕቀፎች 300 ቢሊየን ዶላር እርዳታ አድርጋላች፡፡