ፖለቲካ
ወደ አሜሪካ ያቀኑት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከአሜሪካ ባለስልጣናት ጋር ተወያይተዋል
አሜሪካ የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት ከስምምነተ እንዲደርሱ ሚና ተጫውታለች
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ አሜሪካ ያቀኑት አሜሪካ በዘጋጀችው የአሜሪካ-አፍሪካ መሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ነው
አሜሪካ ባዘጋጀችው የአሜሪካ-አፍሪካ መሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ወደ አሜሪካ ያቀኑት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከአሜሪካ ባለስልጣናት ጋር ተወያይተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትናንትናው እለት ከአሜሪካ ደህንነት አማካሪ ጋር መወያየታቸው ተገልጿል።
ከዚህ በተጨማሪም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ብሊንከን ጋር መወያየታየውን ገልጸዋል።
አሜሪካ በኢትዮጵያ ላለው የሰላም ጥረት ላደረገችው አስዋጽኦ እንደሚያመሰግኑ ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ መንግስት እና በህወሓት መካከል የነበረው ግጭት በሰላም እንዲቋጭ ድርድር እንዲጀመር አሜሪካ ሚና ነበራት።
መንግስትና እና ህወሓት በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት በዘላቂነት ግጭት ለማቆም ስምምነት በደረሱበት ወቅት አሜሪካ የታዛቢነት ሚና ተጫውታለች።
በጦርነቱ ወቅት አሜሪካ፣ የኢትዮጵያ መንግስት ከህወሐት ጋር ለድርድር እንዲቀመጥ ጫና ስታደርግ መቆየቷ ይታወሳል።
ኢትዮጵያ ተጠቃሚ ከሆነችበት ከአጎአ የንግድ ትስስር መሰረዝ እና የማእቀብ እጥላለሁ ማስፈራሪያ ታሰማ ነበር አሜሪካ።