ሩሲያን በኒውክሌር ለማጥቃት የሞከረን ሀገር እንደሚያጠፉ ፕሬዝዳንት ፑቲን ተናገሩ
ፕሬዝዳንት ፑቲን ጥቃትን በመፍራት ቀድሞ ኑክሌር እንደማትተኩስ ገልጸዋል
ፕሬዝዳንት ፑቲን ጥቃትን በመፍራት ቀድሞ ኑክሌር እንደማትተኩስ ገልጸዋል
ሩሲያን በኒውክሌር ጦር ለማጥቃት የሞከረን ሀገር እንደሚያጠፉ ፕሬዝዳንት ፑቲን ተናገሩ።
የምስራቅ አውሮፓ እና እስያ ሀገራት የኢኮኖሚ ጉባኤ በኪርጊስታን በመካሄድ ላይ ሲሆን የዚህ ጉባኤ ተሳታፊ የሆኑት የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ንግግር አድርገዋል።
ፕሬዝዳንት ፑቲን እንዳሉት ሩሲያን በኑክሌር ለማጥቃት የሞከረን ሀገር እንደሚያጠፉ ገልጸዋል።
ሞስኮ የጥቃት ሙከራ ከየትኛውም ሀገር ከተፈጸመባት ያላትን ዘመናዊ ይሀይፐር ሶኒክ ሚሳኤል የሀይል እርምጃ እንደምትወስድ ፕሬዝዳንት ፑቲን ጠቁመዋል።
ይሁንና ሩሲያ በስጋት ምክንያት አስቀድማ የኑክሌር ጥቃት እንደማትሰነዝር ፕሬዝዳንቱ አክለዋል።
ሩሲያ በተጣለባት ማዕቀብ ምክንያት ለአውሮፓ ሀገራት ነዳጅ እያቀረበች አይደለም ያሉት ፕሬዝዳንት ፑቲን በኢሮ-እስያ ሀገራት ላይ ግን የነዳጅ ዋጋ ከሌሎች ሀገራት ጋር ሲነጻጸር በአስር እጥፍ መቀነሱንም አክለዋል።
ሩሲያ በተያዘው ታህሳስ ወር መገባደጃ ቀናት ውስጥ የቀድሞ የሶቪየት ህብረት አባል ሀገራት ጉባኤ በፒተርስበርግ ከተማ ለማድረግ ማቀዷን አስታውቃለች።
የአውሮፓ ህብረት ሩሲያ ነዳጇን በበርሜል ከ60 ዶላር በታች እንዲሸጥ የወሰነውን ውሳኔ ሞስኮ ውድቅ ማድረጓ ይታወሳል።
ሩሲያ የአውሮፓ ህብረትን የነዳጅ ተመንን ለተቀበሉ ሀገራት ነዳጅ እንደማትሸጥ እንዲሁም የአጸፋ እርምጃ ለመውሰድ እየመከረች መሆኗንም ማስታወቋ አይዘነጋም።