ፖለቲካ
ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ ከህወሓት ተደራዳሪ አባላት ጋር ተገናኙ
የመንግስት እና የህወሓት የሰላም ስምምነት ትግበራ አኮሚቴ አባላት ከጠ/ሚ ዐቢይ ጋር ተወያይተዋል
ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ በሰላም ስምምነቱ አፈፃፀም ዙሪያ የተከናወኑ ተግባራት ገምግመዋል
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የሰላም ስምምነት ኮሚቴ አባላት ጋር ተገናኝተው መወያየጣቸው ተነግሯል።
የፌዴራል መንግሥት እና የህወሓት የሰላም ስምምነት ኮሚቴ አባላት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት ለመጀመሪያ ጊዜ በሐላላ ኬላ መገናኘታቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።
በውይይቱ ላይም የህወሓት ተደራዳዎች የሆኑት አቶ ጌታው ረዳ፣ ጄነራል ታደሰ ወረደ፣ ጄነራል ጻቃን እና ሌሎችን የህወሓት ተወካዮች ተሳትፈዋል።
በዚህም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከህወሓትና ከመንግስት የሰላም ስምምነት ትግበራ አስተባባሪ ኮሚቴ ጋር ምክክር አደረገዋል።
በውይይታቸው እስካሁን በሰላም ስምምነቱ አፈፃፀም ዙሪያ የተከናወኑ ተግባራት የተገመገሙ ሲሆን በቀጣይ ትኩረት በሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ላይ አቅጣጫ ተቀምጧል።
የሰላም ድርድሩ ኮሚቴ አስተባባሪዎች ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የመጀመሪያውን የገፅ ለገፅ ግንኙነት ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ጦረትነቱ ከተጀመረ በኋላ ከህወሓት አመራች ጋር በይፋ ሲገናኙ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።