ተመድ የሱዳን ተፋላሚ ኃይሎች ለመደራደር ዝግጁነት አላሳዩም ብሏል
ጠቅላይ ሚኒስተር ዐቢይ አህመድ ከሱዳን ተፋላሚ ኃይሎች ጋር መወያየታቸውን ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒሰትሩ በሱዳን ጦርነት ከተቀሰቀሰ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ከሱዳን ተፋላሚ ኃይሎች ጋር መወያየታቸውን አስታውቀዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከጀነራል አልቡርሃን እና ከጀነራል ደጋሎ ጋር በስልክ መነጋገራቸው ተናግረዋል።
ጀነራል ደጋሎም ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር መነጋገራቸውን ያረጋገጡ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሱዳን ከችግሩ እንድወጣ ድጋፍ አደርጋለሁ ማለታቸውን ገልጸዋል።
በሱዳን፣በሱዳን ጦርና በጀነራል ዳጋሎ በሚመራው ፈጥኖ ደራሽ ኃይል መካከል የተጀመረው ጦርነት ከተቀሰቀሰ ሁለት ሳምንት ገደማ ሆኖታል።
ሁለቱ ተፋላሚ ወገኖች ጦርነቱን እንዲያቆሙ በተደጋጋሚ የቀረበው ጥሪ ሳይሳካ የቆየ ሲሆን በቅርቡ በአማሪካ እና ሳኡዲ አረቢያ አደራዳሪነት የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት በከፊል ተግባራዊ ሆኗል።
በርካታ ሀገራት ዜጎቻቸውን ከሱዳን በማስወጣት ላይ ናቸው።
ከውጭ ሀገራት ዜጎች በተጨማሪ ሰዳናውያንም ሀገራቸውን ለቀው ወደ ተለያዩ ሀገራት እየተሰደዱ ናቸው።
ተመድ የሱዳን ተፋላሚ ኃይሎች ለመደራደር ዝግጁነት አላሳዩም ብሏል።