ፖለቲካ
የሮማው ጳጳስ አባ ፍራንሲስ በዓመታዊ የአምልኮ ስነ-ስርዓት ላይ ለዩክሬን ህዝብ አለቀሱ
አባ ፍራንሲስ በጸሎቱ ክፍል በትክክል መናገር ስላልቻሉ እንባ ሲተናነቃቸው ተስተውሏል
ባለፈው ዓመት የካቲት ወር የጀመረው የሩሲያና ዩክሬን ጦርነት እንደቀጠለ ነው
የሮማው ጳጳስ አባ ፍራንሲስ በዓመታዊ የሀውልት አምልኮ ወቅት ለዩክሬን ህዝብ አልቅሰዋል።
ፖፕ ፍራንሲስ መሀል ሮም “የድንግል ማርያምን የሀውልት አምልኮ” ለማክበር በዓመታዊ የገና ጉብኝት ላይ ለዩክሬን ሰላም ሲጸልዩ አልቅሰዋል።
አባ ፍራንሲስ ወደ ጸሎቱ ክፍል እንደደረሱ በትክክል መናገር ስላልቻሉ በእንባ እየተናነቁ “የዩክሬን ህዝብ ምስጋና ባቀርብልህ ደስ ይለኝ ነበር…” ሲሉ ተደምጠዋል።
በሺህ የሚቆጠሩ ታላላቅ ሊቃነ ጳጳሳት፣ ቀሳውስትና ምእመናን ጳጳሱ በስሜት እንደተሸነፉ ሲረዱ፣ ጭብጨባቸውን ሰብረው እንዲቀጥሉ አበረታተዋል ሲል ዋሽንግተን ፖስት ዘግቧል።
ከረዥም ጊዜ እረፍት በኋላ፤ አባ ፍራንሲስ ካቆሙበት ጸሎቱን በመቀጠል “... የዩክሬን ህዝብ ጌታን ለረጅም ጊዜ ስንጠይቀው ለነበረው ሰላም፤ ይልቁንም ብዙ እየተሰቃዩ ያሉ ህጻናት፣ አዛውንት፣ እናቶችና አባቶች እንዲሁም የዚያች ሰማዕት ሀገር ወጣቶች ልመና ልነግራችሁ ግድ ይለኛል” ብለዋል።
ጳጳሱ ይህን ያሉት “ስፓኒሽ ስቴፕስ” በተባለ ስፍራ ዓመታዊ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት ሲሆን ይህም በፈረንጆቹ ታህሳስ ስምንት ቀን ለኢየሱስ እናት ለማርያም በተሰጠ በዓል ነው።
ዝግጅቱ በጣሊያን የገና ወቅት በይፋ መጀመሩን አመላክቷል ተብሏልም።