የቱርክ ኃይሎች በሶሪያ የምድር ተልዕኮ ለማድረግ መዘጋጀታቸውን ባለስልጣናት ተናገሩ
የቱርክ ጦር ሙሉ ለሙሉ ዝግጁ ለመሆን ጥቂት ቀናት ብቻ እንደሚቀራቸው የአንካራ ሹማምንት ተናግረዋል
የምድር ዘመቻውን ለማካሄድ የፕሬዝዳንቱ ቃል ብቻ እየተጠበቀ መሆኑ ተነግሯል
የቱርክ ጦር በሰሜናዊ ሶሪያ ለምድር ተልዕኮ ለመዘጋጀት ጥቂት ቀናት ብቻ እንደሚያስፈልጉት ተነግሯል።
የቱርክ ባለስልጣናት ጦሩ ድንበር አቋርጦ የኩርድ ታጣቂዎችን በቦምብ ሲደበድብ መቆየቱን ገልጸው፤ ምድረኛ ጦር ለማሰማረት ጫፍ ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ከቱርክ በየቀኑ የሚተኮሱት መሳሪያዎች የኩርድ ኢላማዎችን ለሳምንት ያህል ሲደበድቡና የጦር አውሮፕላኖችም የአየር ድብደባ ሲፈጽሙ መሰንበታቸው ተገልጿል።
ጉዳዩ የተባባሰው ከሁለት ሳምንት በፊት በኢስታንቡል በተፈጸመ ከባድ የቦምብ ጥቃት አንካራ የኩርድ ሚሊሻዎችን ተጠያቂ ካደረገች በኋላ ነው። ታጣቂው በጥቃቱ ውስጥ እጁ እንደሌለበት በመግለጽ ድንበር ተሻጋሪ ጥቃቶችን ምላሽ እየሰጠ ስለመሆኑ ሮይተርስ ዘግቧል።
"የቱርክ ጦር ኃይሎች ሙሉ ለሙሉ ዝግጁ ለመሆን ጥቂት ቀናት ብቻ ያስፈልጋሉ" ያሉት አንድ ከፍተኛ ባለስልጣን፤ የኢስታንቡል ጥቃት ከተፈጸመ ከጥቂት ቀናት በኋላ የቱርክ ደጋፊ የሶሪያ አማፂ ተዋጊዎችም ለዘመቻው ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።
"ተልዕኮውን ለመጀመር ብዙ ጊዜ አይወስድም" ያሉም ሲሆን፤ ትዕዛዙን ፕሬዚዳንቱ ብቻ ይወሰናሉ ብለዋል።
ቱርክ፣ ዩናይትድ ስቴትስ እና የአውሮፓ ህብረት በአሸባሪነት የፈረጁት የኩርዲስታን ሰራተኞች ፓርቲ ክንፍ አድርጋ በምትመለከተው የኩርድ ታጣቂ ቡድን አንካራ በሶሪያ ወታደራዊ ዘመቻ ጀምራለች።
ፕሬዝዳንት ኤርዶጋን ቱርክ ደቡባዊ ድንበሯን ለማስጠበቅ የመሬት ተልዕኮ ትጀምራለች ካሉ ቀናት ተቆጥረዋል።
አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የቱርክ ባለስልጣን ለሮይተርስ "ዝግጅቶች በሙሉ ተጠናቀዋል። የቀረው ፖለቲካዊ ውሳኔ ነው" ሲሉ ተናግረዋል።