
አባ ፍራሲስ በሳምባ ምች ተጠቅተው ሆስፒታል ከገቡ ሁለት ሳምንታት ተቆጥረዋል
የሮማ ካቶሊካዊት ቤት ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳስ አባ ፍራንሲስ የጤና ሁኔታ በሂደት መሻሻሎችን እያሳየ መሆኑን ቫቲካን አስታወቀች።
አባ ፍራንሲስ በተመንፈሻ አካላቸው ላይ ያጋጠማቸውን ህመም ለመታካም ሆስፒታል ከገቡ 14ኛ ቀናቸውን አስቆጥረዋል።
ቫቲካን ዛሬ በሰጠችው መግለጫ፤ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳስ አባ ፍራንሲስ የጤና ሁኔታ ከእለት እለት እየተሻሻለ መምጣቱን አስታውቃለች።
ሆኖም ግን የፊታች ረቡዕ በሚካሄደው የዐቢይ ጾም ማስጀመሪያ ስነ ስርዓትን እንደማይመሩ ቫቲካን ገልጸለች።
ቫቲካን አባ ፍራንሲስ ለምን ያክል ጊዜ ሆስፒታል እንደሚቆዩ ባታሳውቅም፤ ዓመታዊው የረቡዕ የዐቢይ የጾም ማስጀመሪያ ላይ አለመታደማቸው ግን አሁን ሆስፒታል እንደሚቆዩ ያሳያል ተብሏል።
አባ ፍራንሲሰስ በትናትው እለት የተደረገላቸው የምርመራ ውጤት የጤናቸው ሁኔታ መሻሻል እያሳየ መሆኑን ያመለክታል ብላለች ቫቲካን።
ስማቸው እንዳይጠቀስ ያልፈለጉ የቫቲካን ባለስልጣን "አባ ፍራንሲሰስ በጣም ከባድና ውስብስብ የሆነውን ደረጃ አልፈዋል ማለት እንችላለን" ሲሉ ተናግረዋል።
የ88ቱ ሊቀ ጳጳስ አባ ፍራንሲስ ሁለቱም ሳንባቸው በኒሞኒያ ወይም እጥፍ ሳምባ ምች(ደብል ኒሞኒያ) መጠቃት መጀመሩንተከትሎ ነው ሮም በሚገኘው ጀመሊ ሆስፒታል የገቡት።
ደብል ኒሞኒያ በሁለቱም ሳምባዎች ላይ ቃጠሎና ጠባሳ የሚፈጥርና መተንፈስን አስቸጋሪ የሚያደርግ ነው።
የሮማው ጳጳስ አባ ፍራንሲስ በቅርብ አመታት ውስጥ የጤና መቃወስ አጋጥሟቸዋል። ጳጳሱ በወጣነት ዘመናቸው ባጋጠማቸው የሳምባ ምች ምክንያት የተወሰነው የሳምባ ክፍላቸው ተወግዷል።