የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ2024/25 የጨዋታ መርሃግብር ይፋ ሆነ
የአምናው ሻምፒዮን ማንቸስተር ሲቲ በመጀመሪያው ሳምንት በስታምፎርድ ብሪጅ ቼልሲን ይገጥማል
ከ22 አመት በኋላ ወደ ሊጉ የተመለሰው ኢፕስዊች ታውን ደግሞ ሊቨርፑልን በሜዳው ያስተናግዳል
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ2024/25 የውድድር አመት የጨዋታ መርሃ ግብር ዛሬ ይፋ ተደርጓል።
ለአምስተኛ ተከታታይ አመት የሊጉን ዋንጫ ለማንሳት የሚሞክረው ማንቸስተር ሲቲ በመጀመሪያው ሳምንት በስታንፎርድ ብሪጅ ከቼልሲ ጋር ይጫወታል።
ባለፈው የውድድር አመት ሁለተኛ ሆኖ ያጠናቀቀው አርሰናል ደግሞ በኤምሬትስ ወልቭስን ያስተናግዳል።
አርብ ነሃሴ 16 2024 ሊጉ በይፋ ሲጀመር ማንቸስተር ዩናይትድ በኦልትራፎርድ ፉልሃምን ይገጥማል።
ከ22 አመት በኋላ ወደ ሊጉ የተመለሰው ኢፕስዊች ታውን ሊቨርፑልን በሜዳው የሚያስተናግድበት የመጀመሪያ ሳምንት ፍልሚያውም ተጠባቂ ነው።
የ2024/25 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ነሃሴ 16 2024 ተጀምሮ ግንቦት 25 2025 በተመሳሳይ ስአት በሚደረጉ ጨዋታዎችም ፍጻሜውን ያገኛል።
አዳዲስ አሰልጣኞች
አራት የእንግሊዝ ክለቦች አዲስ አስልጣኞችን ቀጥረዋል።
ሊቨርፑል ሆላንዳዊውን አርኔ ስሎት የክሎፕ ተተኪ አድርጓል። ቼልሲም ኢንዞ ማሬስካን አሰልጣኝ አድርጎ ቀጥሯል።
ዌስትሃምና ብራይተንም አዲስ አሰልጣኝ የቀጠሩ ሲሆን፥ ሌስተር የአሰልጣኝ ለውጥ የሚያደርግ አምስተኛው ክለብ ለመሆን ተቃርቧል።
ከእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ሩብ የሚሆኑት የአሰልጣኝ ለውጥ ያደረጉበት የውድድር አመት የፔፕ ጋርዲዮላን ተከታታይ ድል ያስቆም ይሆን?
የመጀመሪያ አምስት ጨዋታዎች
አርሰናል - ከወልቭስ፣ አስቶንቪላ፣ ብራይተን፣ ቶተንሃም እና ማንቸስተር ሲቲ
ማንቸስተር ሲቲ - ከቼልሲ፣ ኢፕስዊች ታውን፣ ዌስትሃም፣ ብሬንትፎርድ እና አርሰናል
ሊቨርፑል - ከኢፕስዊች ታውን፣ ብሬንትፎርድ፣ ማንቸስተር ዩናይትድ፣ ኖቲንግሃም ፎረስት እና በርንማውዝ
ወሳኝ ግጥሚያዎች
ነሃሴ 31 2024
ማንቸስተር ዩናይትድ ከሊቨርፑል
መስከረም 14 2024
ቶትንሃም ከአርሰናል
መስከረም 21 2024
ማንቸስተር ሲቲ ከአርሰናል
ታህሳስ 7 2024
ኤቨርተን ከሊቨርፑል
የካቲት 1 2025
አርሰናል ከማንቸስተር ሲቲ
ሚያዚያ 2 2025
ሊቨርፑል ከኤቨርተን