የሊጉ ኮኮብ ግብ አግቢነትን አርሊንግ ሀላንድ እንደሚያሸንፍ ይጠበቃል
ፊል ፎደን የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የአመቱ ምርጥ ተጨዋቾቸ ተባለ።
ሊጠናቀቅ አንድ ጨዋታ ብቻ የቀረው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አጓጊነቱ እንደቀጠለ ነው።
በሌሎች የአውሮፓ እግር ኳስ ውድድር የዋንጫ አሸናፊዎች ክለቦች ሲታወቁ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ግን አሸናፊውን ለማወቅ እስከ መጨረሻው ጨዋታ ድረስ መጠበቅ የግድ ሆኗል።
ዋንጫውን የማሸነፍ እድል ያላቸው ማንችስተር ሲቲ እና አርሰናል በነገው ዕለት የዓመቱን ስኬት ያውቃሉ።
የሊጉ አወዳዳሪ አካል ከወዲሁ ምርጥ ወጣት ተጫዋች እና ምርጥ የዓመቱ ተጫዋች አሸናፊዎችን ይፋ ሲያደርግ እንግሊዛዊያን አሸናፊ ሆነዋል።
ሲቲን በመልቀቅ ወደ ቸልሲ ያመራው ኮል ፓልመር በምርጥ ቀጣት ተጫዋችነት ሲመረጥ ሌላኛው እንግሊዛዊ የማንችስተር ሲቲው ፊል ፎደን ደግሞ የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች ተብሎ ተመርጧል።
ፊል ፎደን በዘንድሮው የውድድር አመት በሊጉ ለማንችስተር ሲቱ አስራ ሰባት ግቦችን ሲያስቆጥር ስምንት ለግብ የሆኑ ኳሶችንም አመቻችቶ ያቀበለ ሲሆን ሁለት ሀትሪክም ሰርቷል።
የ2023/24 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ምርጥ አሰልጣኝ እና ኮኮብ ግብ አግቢ ነገ እንደሚታወቁ ስካይ ስፖርት ዘግቧል።
በምርጥ አሰልጣኝነት እጩ ከሆኑ አሰልጣኞች መካከል ስፔናዊያኑ የማንችስተር ሲቲው አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ እና የአርሰናሉ ሚካኤል አርቴታ የማሸነፍ እድላቸው ከፍተኛ ነውም ተብሏል።