የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ሙሃሙድ ቡሃሪ ከሀገሪቱ ምርጫ አስቀድሞ አዲስ የሽግግር ስርዓት አዘጋጁ
ከአንዱ የፕሬዝዳንት አስተዳደር ወደ አዲሱ አስተዳደር የስልጣን ሽግግር ያለምንም እንከን እንዲተላለፍ የሚያደርግ የህግ ማዕቀፍ ነው የተዘጋጀው
የፊታችን ግንቦት 29 አዲሱ የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ቃለ መሃላ ይፈጸማሉ ተብሎ ይጠበቃል
የናይጄሪያው ፕሬዝዳንት ሙሃማዱ ቡሃሪ ከፈረንጆቹ የካቲት 25 ምርጫ በኋላ ለሚመጣው አዲስ ፕሬዝዳንት ሽግግርን ለማመቻቸት ተዘጋጅተዋል ተብሏል።
ፕሬዝዳንቱ ለሽግግሩ ምክር ቤት የሚያቋቁም የስራ አስፈጻሚ ትዕዛዝ ፈርመዋል።
የ80 ዓመቱ ቡሃሪ በህገ-መንግስቱ መሰረት በምርጫው መሳተፍ የማይችሉ ሲሆን፤ ሁለተኛና የመጨረሻ የስልጣን ዘመናቸውን በማገልገል ላይ ይገኛሉ።
በፈረንጆቹ 1999 የናይጄሪያ ወታደራዊ አገዛዝ ካበቃ በኋላ ሁለት ዓመት የስልጣን ዘመናቸውን ያጠናቀቁ ሁለተኛው የናይጄሪያ መሪ ሆነዋል።
በመጭው ግንቦት 29 አዲሱ የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ቃለ መሃላ ይፈጸማሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ቡሃሪ በሰጡት መግለጫ "አዲሱ የስራ አስፈጻሚ ትዕዛዝ ከአንዱ የፕሬዝዳንት አስተዳደር ወደ አዲሱ አስተዳደር የስልጣን ሽግግር ያለምንም እንከን እንዲተላለፍ የሚያደርግ የህግ ማዕቀፍ ተዘጋጅቷል" ብለዋል።
የፊታችን ማክሰኞ የሚጀመረውን የሽግግር ምክር ቤት የናይጄሪያ የፌዴሬሽን ጸሃፊ ይመሩታል ማለታቸውንም ሮይተርስ ዘግቧል።
ቡሃሪን ለመተካት የሚወዳደሩት ሦስት ዋና ዋና እጩዎች ቦላ ቲኒፉ ከገዥው ፓርቲ፣ ከዋናው ተቃዋሚ ፓርቲ አቲኩ አቡበከር እና ከሌላ ትንሽ ፓርቲ ፒተር ኦቢ ናቸው ተብሏል።