ሀገራቱ ከፈረንጆች 2021 ወዲህ ግንኙነታቸውን ለማደስ እየተንቀሳቀሱ ነው
የግብጽ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሳሚ ሹክሪ በዚህ ሳምንት ቱርክን ዳግም ሊጎበኙ እንደሚችሉ ተነግሯል።
ጉብኙቱን ያሳወቀው የአንካራ መንግስት ሀገራቱ ከአስር ዓመታት በፊት ግንኙነታቸው ከተቋረጠ በኋላ ልዑካንን ዳግም ለመመለስ የግንኙነት መሻሻል ሊደረግ እንደሚችል ገልጿል።
የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሜቭሉት ካቩሶግሉ ሳሚ ሹክሪ በዚህ ሳምንት አንካራ ይገባሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተናግረዋል።
እስካሁን የጉብኝቱ ዝርዝር ይፋ አልተደረገም።
ተጨባጭ እርምጃዎችን ለመውሰድ ጊዜው አሁን ነውም ብለዋል።
"በጉብኝቱ አምባሳደሮችን ለመሾም እርምጃዎችን መውሰድ እንችላለን" ብለዋል።
የቀድሞው የግብጽ ፕሬዝዳንት እና የአንካራ አጋር መሀመድ ሙርሲ ከስልጣን መውረድን ተከትሎ የሀገራቱ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸው ከተቋረጠ ከአስር አመታት በኋላ ካቩሶግሉ ባለፈው ወር ካይሮን ጎብኝተዋል።
ሹክሪ በቱርክ እና ሶሪያ ከ50 ሽህ በላይ ሰዎችን ከገደለው ግዙፍ የመሬት መንቀጥቀጥ በኋላ አጋርነትን ለማሳየት ቱርክን ጎብኝተዋል።
ሹክሪ አምባሳደሮችን መመለስ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ በተገቢው ጊዜ ውይይት እንደሚካሄድ ተናግረዋል።
በአንካራና ካይሮ መካከለሰ ግንኙነትን ለመመለስ መነጋገር የተጀመረው በፈረንጆች 2021 እንደሆነ ሮይተርስ ዘግቧል።
ነገር ግን የግብጽ ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ አልሲሲ እና የቱርኩ አቻቸው ጣይብ ኤርዶጋን በዶሃ ዓለም ዋንጫ ከተጨባበጡ በኋላ በአንካራ እና በካይሮ መካከል ግንኙነት በመደበኛነት ለመመለስ እንቅስቃሴዎች ተፋጥነዋል።
ከግንቦቱ የቱርክ ምርጫ በኋላ ፕሬዚዳንቶቹ በአካል ሊገናኙ እንደሚችሉም ካቩሶግሉ ተናግረዋል።