ልዩልዩ
የፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴን ጨምሮ ሶስት የአፍሪካ መሪዎች ስዕል በፓሪስ ለእይታ ቀረበ
ታዋቂው ሰዓሊ ኪንዴ ዊሊ የስዕል አውደ ርዕዩን በፓሪስ ለአራት ወራት ለጎብኚዎች ያቀርባል ተብሏል
ሰዓሊ ዊሊ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማን በመሳል በመላው ዓለም አድናቆትን አግኝቶ ነበር
የፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴን ጨምሮ ሶስት የአፍሪካ መሪዎች ስዕል በፓሪስ ለእይታ ቀረበ።
የ46 ዓመቱ ሰዓሊ ዊሊ የሰዎችን ስዕል ከእውነተኛ ገጽታቸው እና መልካቸው ጋር አመሳስሎ በመሳል ታዋቂነትን አትርፏል።
የጥቁር መሪዎችን በመሳል የሚታወቀው ይህ ሰዓሊ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴን ጨምሮ የአፍሪካ መሪዎችን ስዕል መሳሉን አስታውቋል።
በአሜሪካ ታሪክ የመጀመሪያው ጥቁር ፕሬዝዳንት የሆኑት ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማን ስዕል በፈረንጆቹ 2018 ላይ በመሳል አድናቆትንም አግኝቷል ሰዓሊ ዊሊ።
ይህ ስዕል የተሳለበት ጥበብ እና ውበት በበርካቶች እንዲደነቅ አድርጎትም ነበር።
አሁን ደግሞ ከፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በተጨማሪ የጋናው ፕሬዚዳንት ናና አኩፎ አዱ እና የቀድሞው የናይጀሪያ ፕሬዝዳንት ኦሊሴጎኖ ኦባሳንጆን ስዕል መሳሉን ቢቢሲ ዘግቧል።
የነዚህ የአፍሪካ መሪዎች ስዕል ለቀጣዮች አራት ወራት በፈረንሳይ መዲና ፓሪስ በሚቆይ የስዕል አውደርዕይ ላይ ለጎብኝዎች ይቀርባል ተብሏል።
ሰዓሊ ዊሊ ስለ አዲሱ ስዕሎቹ በተዘጋጀ ዘጋቢ ፊልም ላይ እንዳለው ስዕሎቹን ለመሳል 10 ዓመት እንደፈጀበት ተናግሯል።